Loading
Singer
የትንሳኤው ፡ ጀግና ፡ ነው የትንሳኤው ፡ ንጉሥ ሕያው ፡ ሆኖ ፡ ተነሳ ፡ መሬቱ ፡ ሳይማስ ሕያው ፡ ሆኖ ፡ ተነስቷል ፡ መቃብር ፡ ሳይማስ የሞትን ፡ መውጊያ ፡ ሰብሮ ፡ ሲዖልን ፡ ድል ፡ ነሳ ሕይወቱን ፡ ዋጋ ፡ ከፍሎ ፡ ለተጎዳው ፡ ካሳ ይገርመኛል (፪x) ዝም ፡ ብሎ ፡ ይገርመኛል ይደንቀኛል (፪x) ዝም ፡ ብሎ ፡ ይደንቀኛል ሰማቹ ፡ ወይ ፡ ቀና ወሬ ሰማችሁ ፡ ወይ ፡ መልካም ፡ ዜና የሞተው ፡ ተነስቷል ፡ ተብሎ ፡ ሲወራ ከመሬት ፡ በላይ (፫x) በላይ አልቻለውም ፡ ሊይዘው አልቻለውም ፡ ሊያስቀረው መቃብሩ ፡ ሲከፈት ፡ውጡ ባዶ ፡ ነው የእኔ ፡ ጌታ ፡ የእኔ ፡ ንጉሥ ፡ ወደላይ ፡ ያረገው ይሄ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ከሌሎቹ ፡ ልዩ ፡ የሚያደርገው ኤልሻዳይ ፡ ነው አዶናይ ፡ ነው ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነው ኤማኦስም ፡ አልወርድም ፡ ቁርጤንም ፡ ሳልሰማ መቃብር ፡ ውስጥ ፡ ቢሆንም ፡ ድምጽ ፡ አለ ፡ ሚሰማ ሲስት ፡ ቀን ፡ ሶስት ፡ ለሊት ፡ መሬት ፡ ውስጥ ፡ ቢያድርም እነሳለሁ ፡ ስላለ ፡ ተሸነፈ ፡ አልልም