Loading
Singer
በውስጥህ ፡ እሳቴን ፡ አቀጣጥላለሁ የኃጢአትንም ፡ ዱር ፡ ጫካን ፡ እገልጣለሁ ነበልባሉ ፡ አይጠፋም ፡ ይነዳል ፡ ጨምሮ ሰሜኑን ፡ ይበላል ፡ ከደቡብ ፡ ጀምሮ ነውረኛውን ፡ ነገር ፡ ፈጽሞ ፡ እስኪያጠፋ የነበልባሉን ፡ ኃይል ፡ ማነው ፡ የሚያጠፋ ብቻ ፡ አንተ ፡ ተቀደስ ፡ ከነውር ፡ ተለይ ክብሬ ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ሊገለጥ ፡ ሊታይ አዝ፦ ተነስ ፡ አንተ ፡ ትውልድ ፡ ተነስ (፪x) እቃ ፡ ጦርህን ፡ በአግባቡ ፡ ልበስ ያልታረሰውን ፡ ድንግሉን ፡ ለማረስ ጫማህን ፡ አጥልቅ ፡ ተነስ አንተ ፡ ተውልድ ፡ ተነስ ብዙ ፡ ስራ ፡ አለኝ ፡ በአንተ ፡ የምሰራው በመጀመሪያ ፡ ግን ፡ ቤቴን ፡ ነው ፡ ማጠራው እንዳትሆንብኝ ፡ ጥፋት ፡ ከሚያገኘው ዛሬ ፡ ቀን ፡ እያለ ፡ ተጠንቀቅ ፡ እልሃለሁ ይሄን ፡ ድምጼን ፡ ሰምተህ ፡ ቢቀናህ ፡ መንገድህ በምሰራበት ፡ ቀን ፡ ገንዘብ ፡ ትሆናለህ ሰባራውን ፡ ጠጋኝ ፡ አጋዥ ፡ ትባላለህ ድል ፡ ነሺ ፡ በመሆን ፡ ደግሞም ፡ ትከብራለህ አዝ፦ ተነስ ፡ አንተ ፡ ትውልድ ፡ ተነስ (፪x) እቃ ፡ ጦርህን ፡ በአግባቡ ፡ ልበስ ያልታረሰውን ፡ ድንግሉን ፡ ለማረስ ጫማህን ፡ አጥልቅ ፡ ተነስ አንተ ፡ ተውልድ ፡ ተነስ የተጠራህበት ፡ ጥሪ ፡ ይህ ፡ ነውና ስራዬን ፡ ልትሰራ ፡ ጊዜው ፡ ቀርቧልና ቃሌን ፡ በደምብ ፡ ብላ ፡ በአግባቡ ፡ ጸልይ ሃሳቤ ፡ ይፈጸማል ፡ ያለው ፡ በሰማይ በምድር ፡ አምባሳደር ፡ ተወካዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ስራዬን ፡ ለመስራት ፡ ከልብ ፡ ከተሰጠህ መጨረሻው ፡ ደርሷል ፡ የምገለጥበት ለሁሉም ፡ እንደስራው ፡ ዋጋ ፡ ምከፍልበት አዝ፦ ተነስ ፡ አንተ ፡ ትውልድ ፡ ተነስ (፪x) እቃ ፡ ጦርህን ፡ በአግባቡ ፡ ልበስ ያልታረሰውን ፡ ድንግሉን ፡ ለማረስ ጫማህን ፡ አጥልቅ ፡ ተነስ አንተ ፡ ተውልድ ፡ ተነስ