Loading
Singer
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ በዙፋኑ ፡ ነው (ሆ) ስሙ ፡ ሲጠራ ፡ ይሰራል ፡ አየነው ፡ ይኸው (ሆ) በጌትነቱ ፡ ችሎት ፡ አምኖ ፡ ሚስማማ እርሱ ፡ አምላኬ ፡ ነው ፡ የሚል ፡ ድምጹን ፡ ያሰማ (፪x) አዝ፦ ተነስ ፡ በገና ፡ ሆይ ፡ ተነስ ፤ ተነስ ፡ ማሲንቆ ፡ ሆይ ፡ ተነስ ተነስ ፡ እኔም ፡ እነሳለሁ ፤ ተነስ ፡ አምላኬ ፡ እንዲወደስ ተነስ ፡ ወንድሜ ፡ ሆይ ፡ ተነስ ፤ ተነሽ ፡ እህቴ ፡ ሆይ ፡ ተነሽ ተነሽ ፡ እኔም ፡ እነሳለሁ ፤ ተነሽ ፡ አምላኬ ፡ እንዲወደስ ይሰማ ፡ አዳዲስ ፡ ዜማ ፡ በድል ፡ ቀን ፡ የግል ፡ ዝማሬ እንደተባለው ፡ አልሆነም ፡ ውሸት ፡ ነው ፡ የጠላት ፡ ወሬ የእኛ ፡ አምላክ ፡ ስሙ ፡ ሲጠራ ፡ ከሰማይ ፡ በእሳት ፡ መልሷል ይህንን ፡ የሰማ ፡ ያያ ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ችሎ ፡ ይቀመጣል አዝ፦ ተነስ ፡ በገና ፡ ሆይ ፡ ተነስ ፤ ተነስ ፡ ማሲንቆ ፡ ሆይ ፡ ተነስ ተነስ ፡ እኔም ፡ እነሳለሁ ፤ ተነስ ፡ አምላኬ ፡ እንዲወደስ ተነስ ፡ ወንድሜ ፡ ሆይ ፡ ተነስ ፤ ተነሽ ፡ እህቴ ፡ ሆይ ፡ ተነሽ ተነሽ ፡ እኔም ፡ እነሳለሁ ፤ ተነሽ ፡ አምላኬ ፡ እንዲወደስ ተነስ! በልዑል ፡ መጠጊያ ፡ የሚኖር ፡ ሁሉን ፡ በሚችል ፡ አምላክ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ያድራል ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ያድራል እግዚአብሔርን ፡ አንተ ፡ መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ እለዋለሁ አምላኬና ፡ መሸሸጊያዬ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ እታመናለሁ እርሱ ፡ ከአዳኝ ፡ ወጥመድ ፡ ከሚያስደነግጠው ፡ ነገር ፡ ያድናል በላባዎቹ ፡ በላባዎቹ ፡ ይጋርደኛል በክንፎቹ ፡ በታች ፡ ትተማመናለች ፡ እውነት (፫x) ፡ እውነት ፡ እንደጋሻ (፪x) ፡ ይከብበኛል??? በሌሊት ፡ ግርማ ፡ በቀን ፡ ከሚበር ፡ ፍላጻ በጨለማ ፡ ከሚሄድ ፡ ክፉ ፡ ነገር ከአደጋና ፡ ከቀትር ፡ ጋኔን ፡ አትፈራም በአተገብህ ፡ ሺ ፡ በቀኝህ ፡ አስር ፡ ሺ ፡ ይወድቃሉ ወደአንተ ፡ ግን ፡ አይቀርቡም በዐይኖችህ ፡ ብቻ ፡ ትመለከታለህ የሃጢአንን ፡ ብድራት (፪x) ፡ ታያለህ አቤቱ ፡ አንተ ፡ ተስፋዬ ፡ ነህ ፡ ልዑልን ፡ መጠጊያ ፡ ያደረጉ ክፉ ፡ ነገር ፡ ወደአንተ ፡ አይቀርብም ፡ መቅሰፍትም ፡ ወደ ፡ ቤትህ ፡ አይገባም በመንገድህ ፡ ይጠብቁህ ፡ ዘንድ ፡ መልአክትን ፡ ስለአንተ ፡ ያዛቸዋል እግርህን ፡ በድንጋይ ፡ እንዳትሰናከል ፡ በእጆቻቸው ፡ ያነሱሃል በተኩላና ፡ በእባብ ፡ ላይ ፡ ትጫማለህ ፡ አንበሳውና ፡ ዘንዶውን ፡ ትረግጣለህ በእኔ ፡ ተማምኗልና ፡ አስጥለዋለሁ ፡ ስሜን ፡ አውቋልና ፡ እጋርደዋለሁ የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ በዙፋኑ ፡ ነው (ሆ) ስሙ ፡ ሲጠራ ፡ ይሰራል ፡ አየነው ፡ ይኸው (ሆ) በጌትነቱ ፡ ችሎት ፡ አምኖ ፡ ሚስማማ እርሱ ፡ አምላኬ ፡ ነው ፡ የሚል ፡ ድምጹን ፡ ያሰማ (፪x) አዝ፦ ተነስ ፡ በገና ፡ ሆይ ፡ ተነስ ፤ ተነስ ፡ ማሲንቆ ፡ ሆይ ፡ ተነስ ተነስ ፡ እኔም ፡ እነሳለሁ ፤ ተነስ ፡ አምላኬ ፡ እንዲወደስ ተነስ ፡ ወንድሜ ፡ ሆይ ፡ ተነስ ፤ ተነሽ ፡ እህቴ ፡ ሆይ ፡ ተነሽ ተነሽ ፡ እኔም ፡ እነሳለሁ ፤ ተነሽ ፡ አምላኬ ፡ እንዲወደስ የአህዛብ ፡ አማልክት ፡ በድኖች ፡ አይሰሙ ፡ ጆሮ ፡ እያላቸው ይጥሩት (፬x) ፡ ተኝቶ ፡ ይሆን ፡ አምላካቸው የእኔ ፡ ግን ፡ አምላክ ፡ ግን ፡ የኤልያስ ፡ ስጠራው ፡ ከላይ ፡ የሰማኝ ተማምኜው ፡ ልኑር ፡ እንጂ ፡ አምኜው ፡ ሥጋት ፡ አይገባኝ አዝ፦ ተነስ ፡ በገና ፡ ሆይ ፡ ተነስ ፤ ተነስ ፡ ማሲንቆ ፡ ሆይ ፡ ተነስ ተነስ ፡ እኔም ፡ እነሳለሁ ፤ ተነስ ፡ አምላኬ ፡ እንዲወደስ ተነስ ፡ ወንድሜ ፡ ሆይ ፡ ተነስ ፤ ተነሽ ፡ እህቴ ፡ ሆይ ፡ ተነሽ ተነሽ ፡ እኔም ፡ እነሳለሁ ፤ ተነሽ ፡ አምላኬ ፡ እንዲወደስ (፪x)