Loading
Singer
ደስታችን ፡ በምድር ፡ ፍፁም ፡ ባይሆን ፡ እንኳን ልባችን ፡ ሲመታ ፡ በመከራ ፡ ሃዘን የጌታን ፡ መገለጥ ፡ በመጠበቃችን የምንጽናናበት ፡ አዲስ ፡ አገር ፡ አለን አዝ፦ ተንቀን ፡ አንቀርም ፡ ተጥለን ፡ በምድር አዲስ ፡ አገር ፡ አለን ፡ ከአድማስ ፡ ባሻገር ጌታም ፡ ይመለሳል ፡ ዳግም ፡ ሊያሳርፈን በገዛ ፡ ዙፋኑ ፡ በቀኝ ፡ ሊያስቀምጠን የምድር ፡ መጽዐተኛ ፡ ባለ ፡ ፅኑ ፡ ተስፋ በላይ ፡ ያለው ፡ ሽቶ ፡ በምድር ፡ የተገፋ ባይደላውም ፡ እንኳን ፡ ፀንቶ ፡ በመታገስ በክብር ፡ ያየዋል ፡ የናፈቀውን ፡ ንጉሥ አዝ፦ ተንቀን ፡ አንቀርም ፡ ተጥለን ፡ በምድር አዲስ ፡ አገር ፡ አለን ፡ ከአድማስ ፡ ባሻገር ጌታም ፡ ይመለሳል ፡ ዳግም ፡ ሊያሳርፈን በማያልፈው ፡ መንግሥት ፡ ዘለዓለም ፡ ሊያነግሰን የዚህን ፡ ዓለም ፡ ሃሳብ ፡ ታግሎ ፡ ያሸነፈ በመከራ ፡ ፀንቶ ፡ በትዕግሥት ፡ ያለፈ አምላኩ ፡ ሲገለጥ ፡ እጅጉን ፡ ይፅናናል ያልተሰማ ፡ ዜማን ፡ ውዳሴን ፡ ያፈልቃል አዝ፦ ተንቀን ፡ አንቀርም ፡ ተጥለን ፡ በምድር አዲስ ፡ አገር ፡ አለን ፡ ከአድማስ ፡ ባሻገር ጌታም ፡ ይመለሳል ፡ ዳግም ፡ ሊያሳርፈን በማያልፈው ፡ መንግሥት ፡ ዘለዓለም ፡ ሊያነግሰን መከራም ፡ ይረሳል ፡ ሃዘንም ፡ ይቀራል ያናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ እምባችንን ፡ ያብሳል ጻድቅ ፡ ፈራጃችን ፡ በቅርብ ፡ ይገለጣል የወጉትም ፡ ዐይኖች ፡ ፊት ፡ ለፊት ፡ ያዩታል አዝ፦ ተንቀን ፡ አንቀርም ፡ ተጥለን ፡ በምድር አዲስ ፡ አገር ፡ አለን ፡ ከአድማስ ፡ ባሻገር ጌታም ፡ ይመለሳል ፡ ዳግም ፡ ሊያሳርፈን በገዛ ፡ ዙፋኑ ፡ በቀኝ ፡ ሊያስቀምጠን (፪x)