Loading
ባነበብን ፡ ቁጥር ፡ ባወቅነው ፡ የማንለምደው ፡ ቃልህን በገባን ፡ ቁጥር ፡ ባወቅነው ፡ ምንፈልገው ፡ ቃልህን ፡ ነው ዛሬም ፡ እንድትልልን ፡ ሳይሆን ፡ ልትል ፡ ያሰብከው ፡ ያግኘን ያለመከልከል ፡ ተናግረህ ፡ ያለገደብ ፡ ስራብን መንፈስህ ፡ ይግዛን ፡ ይስፈንብን ፡ በሙላት የልብህ ፡ ሀሳብ ፡ ያጥምደን ፡ የሚያቆመን ፡ ያ ፡ ነው ፡ በጽናት እናድጋለን ፡ እንጂ ፡ ሰርክ ፡ ወዳንተ ልናድግ ፡ አይቻለንም ፡ ባንተ ፡ ላይ ከፍለን ፡ ባወቅንህ ፡ ቁጥር ዝቅ ፡ እንበል ፡ እንይ ፡ ወደላይ ምን ፡ ብናውቅ ፡ ጥበብ ፡ ቢጠጋን ሲመስለን ፡ ያወቅን ፡ የበቃን አናውቅም ፡ ባወቅን ፡ ቁጥር ደቀ ፡ መዝሙር ፡ ነን ፡ ሁሌ ፡ ባንተ ፡ ስር ተማሪዎች ፡ ነን ፡ ሁሌ ፡ ልጆችህ መቼም ፡ በማንጨርሰው ፡ ትምህርትህ ከፍለን ፡ ባወቅን ፡ ጥቂት ትሁት ፡ አድርገን ፡ ባንተ ፡ ፊት ታማኝ ፡ አድርገን ፡ ለቃልህ አቅናን ፡ ለውድ ፡ ሀሳብህ መስታወት ፡ በሆነው ፡ ቃልህ አብቃን ፡ ለልብ ፡ መንገድህ ተናገር ፡ ኢየሱስ ተናገር ፡ በሀይል ፡ እንሰማሀለን ተናገር ፡ መንፈስቅዱስ ተናገር ፡ በሙላት ፡ እንሰማሀለን ተናገር ፡ እንሰማሀለን
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.