Loading
Singer
ተመስገን ፡ ነው ፡ ያለኝ ፡ ለዚህ ፡ ለጌታዬ እለት ፡ እለት ፡ በዝቷል ፡ ምህረቱ ፡ በላዬ ተመስገን ፡ ነው ፡ ያለኝ ፡ ለዚህ ፡ ለጌታዬ እለት ፡ እለት ፡ በዝቷል ፡ ምህረቱ ፡ በላዬ ለዚህ ፡ ሁሉ ፡ ሰላም ፡ ለዚህ ፡ ሁሉ ፡ እረፍት አንድም ፡ ነገር ፡ የለም ፡ እኔ ፡ የከፈልኩት የሰጠኸኝ ፡ ሁሉ ፡ ተገብቶኝ ፡ አይደለም ምህረትህ ፡ በዝቶ ፡ ነው ፡ ክበር ፡ ለዘላላም ቅዱሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆንህ ፡ ከኔ ፡ ጋራ ከቅዱሳንም ፡ ጋር ፡ አረከኝ ፡ ምጠራህ ለዚህ ፡ ያደረሰከኝ ፡ ኧረ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነኝ ምረትህ ፡ በዝቶ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ክብረልኝ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምን ፡ አለ ፡ የሚያስደንቅ ፡ ነገር አንተ ፡ ከሰው ፡ ጋራ ፡ ከመሆንህ ፡ በቀር ምታስፈልገውን ፡ አንድም ፡ የሆንከውን አምላኬ ፡ ተመስገን ፡ አግኝቻለሁ ፡ አንተን በስምህ ፡ ባሕሩን ፡ ከፍለህ ፡ አሻግረኸኛል ከጠላትም ፡ ወጥመድ ፡ አስመልጠኸኛል እዚህ ፡ የደረስኩት ፡ በአንተ ፡ ጥበቃ ፡ ነው ለበዛው ፡ ምህረትህ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኸው