Loading
Singer
አዝ፦ ተመሥገን ፡ ጌታዬ ክብር ፡ ገናንነት ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን ተመሥገን ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ክብር ፡ ገናንነት ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን (፪x) በጉለት ፡ እንዲቆይ ፡ ሳይደክም ፡ ጉልበቴ ኃይልን ፡ አስታጠቀኝ ፡ ከላይ ፡ መድኃኒቴ በብዙ ፡ ውሽንፍር ፡ ቢያጥለቀልቅ ፡ ጐርፉ ጠላቶች ፡ በአንተ ፡ ሥም ፡ ሁሉም ፡ ተሸነፉ አዝ፦ ተመሥገን ፡ ጌታዬ ክብር ፡ ገናንነት ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን ተመሥገን ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ክብር ፡ ገናንነት ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን (፪x) የኑሮዬ ፡ ተገን ፡ ክብሬ ፡ መከታዬ ኃይሌም ፡ ይታደሳል ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ተድላዬ ማዕበሉ ፡ ተነስቶ ፡ ሊያሰጥመኝ ፡ ሲቃጣ በገሀድ ፡ አያለሁ ፡ ረዳቴ ፡ ስትመጣ አዝ፦ ተመሥገን ፡ ጌታዬ ክብር ፡ ገናንነት ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን ተመሥገን ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ክብር ፡ ገናንነት ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን (፪x) የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት ፡ አያልቅም ፡ ቢቆጠር ነነዌም ፡ ብትሰራ ፡ ኃጢአት ፡ በማግበስበስ አምላክም ፡ አስቦ ፡ እነርሱን ፡ ለመምከር አዘዘው ፡ ዮናስን ፡ ለሕዝቡ ፡ እንዲናገር አዝ፦ ተመሥገን ፡ ጌታዬ ክብር ፡ ገናንነት ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን ተመሥገን ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ክብር ፡ ገናንነት ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን (፪x)