Loading
Singer
ተመሥገን (፲x) ከአብ ፡ ዘንድ ፡ ያለኸኝ ፡ ለእኔ ፡ ጠበቃዬ በፍቅር ፡ የምታየኝ ፡ ወዳጅ ፡ አፍቃሪዬ ፈልጌ ፡ የማላጣህ ፡ የምትቆም ፡ ከጐኔ አንተ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ ድጋፍ ፡ መከታዬ (፪x) ልዩ ፡ ወዳጄ ፡ ነህ ፡ ቋሚ ፡ ተጠሪዬ ለሚደርስብኝም ፡ ነህ ፡ ተቆርቋሪዬ ከእኔ ፡ የማትለይ ፡ የማትጠፋ ፡ ከጐኔ አንተ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ ተሟጋች ፡ ለነፍሴ (፪x) ተመሥገን (፲x) ከገመትኩት ፡ በላይ ፡ ፍቅሩ ፡ ለእኔ ፡ በዛ ፍፁም ፡ አይገመት ፡ እንዲህ ፡ እንደ ፡ ዋዛ ግርዶሼን ፡ ቀደደው ፡ ልጁን ፡ አድርጐ ፡ ቤዛ እግዚአብሔር ፡ ወደደኝ ፡ በፍቅሩ ፡ እኔን ፡ ገዛ (፪x) ፍቅሩ ፡ እጅግ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ከሁሉም ፡ የሚስብ ያየ ፡ የሰማውን ፡ እጅግ ፡ የሚያስደንቅ በከበረው ፡ ዙፋን ፡ ነፍሴን ፡ አኖረልኝ ሁሉንም ፡ ድል ፡ አድርጐ ፡ ድል ፡ አወጀልኝ (፪x) ተመሥገን (፲x) መላእክት ፡ ተደፍተው ፡ ለሚሰግዱልህ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ብለው ፡ ለሚያዜሙልህ እኔም ፡ ተነስቼ ፡ ቅዱስ ፡ ነህ ፡ እላለሁ ከእግርህ ፡ ሥር ፡ ወድቄ ፡ ክብርን ፡ እሰጣለሁ (፪x) በዕልልታ ፡ ሽብሸባ ፡ ቤትህ ፡ እገባለሁ ሁሌም ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ እገዛልሃለሁ ለአንተ ፡ የሚሳንህ ፡ አላየሁምና ዛሬም ፡ እልሃለሁ ፡ ይብዛልህ ፡ ምሥጋና ዛሬም ፡ ነገም ፡ ለአንተ ፡ ይብዛልህ ፡ ምሥጋና (፪x) ተመሥገን (፲x)