Loading
Singer
አዝ፦ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ተመስገን ተመስገን ፡ አምላኬ ፡ ተመስገን (፬x) እንደ ፡ እናት ፡ በጀርባ ፡ አዝለህ ፡ አሳደግከኝ ክፉም ፡ እንዳይነካኝ ፡ በእጅግ ፡ ሰወርከኝ ውበት ፡ ደም ፡ ግባቴ ፡ ሞገሴ ፡ ሆንክልኝ እኔም ፡ ዝም ፡ አልልም ፡ ለአንተ ፡ አዜማለሁኝ አዝ፦ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ተመስገን ተመስገን ፡ አምላኬ ፡ ተመስገን (፬x) ሁልጊዜ ፡ ሳስበው ፡ ለኔ ፡ ያደረከውን ቃላቶች ፡ ያጥሩኛል ፡ አንተን ፡ ለማመስገን በብዙ ፡ ሃጥያቴ ፡ ዘወትር ፡ ሳስቸግርህ በፊትህ ፡ አልጣልከኝም ፡ አምላኬ ፡ አቆመኝ ፡ ምህረትህ አዝ፦ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ተመስገን ተመስገን ፡ አምላኬ ፡ ተመስገን (፬x) ብዙ ፡ ማይታለፍ ፡ ተራራ ፡ ሸለቆ አምላኬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ያሳለፍከኝ ፡ እኮ እኔስ ፡ የአንተ ፡ ውለታ ፡ ከልቤ ፡ አይጠፋም ሁሌ ፡ አዜመዋለሁ ፡ ላፍታ ፡ ዝም ፡ አልልም አዝ፦ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ተመስገን ተመስገን ፡ አምላኬ ፡ ተመስገን (፬x) ለዓለም ፡ ለሚመጣው ፡ ትውልድ ፡ አወራለሁ ያደረክልኝን ፡ እመሰክራለሁ ብዙ ፡ ዘመናትን ፡ ወራት ፡ ዓመታትን በእራሴ ፡ አይደለም ፡ ያለፍኩት ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ ተመስገን አዝ፦ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ተመስገን ተመስገን ፡ አምላኬ ፡ ተመስገን (፪x)