Loading
አግዘኝ ፡ ደግፈኝ ፡ ብዬ ፡ ነበረ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሰማኸኝ ፡ ስለቴም ፡ ሰመረ ብዬ ፡ እልሃለው ፡ እንደገና በአዲስ ፡ ዝማሬ ፡ በአዲስ ፡ ዜማ የአየሁትን ፡ በዓይኔ ፡ አይቻለሁ እጅህን ፡ በብዙ ፡ አይቻለሁ ምሥጋናዬ ፡ በፊትህ ፡ ያርግልኝ አምልኮዬ ፡ በፊትህ ፡ ይፍሰስልኝ ዝማሬ ፡ በፊትህ ፡ ሞገስ ፡ ያግኝልኝ አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ ፡ ረዳቴ በጭንቅ ፡ ዘመን ፡ እረፍቴ በማያምር ፡ ቀን ፡ ወበት ፡ ድምቀቴ የደስታዬ ፡ ድምጽ ፡ ጩኸቴ (፪x) የለኝም ፡ ሌላ ፡ እኔ ፡ የምለዉ ይሄ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ እንኳን ፡ የማነሳው ፡ ከሰው የድስታዬ ፡ ቀኑ ፡ ባለቤት ብቻህን ፡ ታይበት ፡ ይህን ፡ ነው ፡ የምለው ተመሥገን ፣ ተመሥገን (፰x) አዘኑ ፡ ክፉ ፡ ያዩልኝ ፡ ቀኖቼ እንባን ፡ የሻቱ ፡ ለዓይኖቼ ቀኔን ፡ አዘኸው ፡ ከላይ ፡ ከሠማይ ጠገብኩ ፡ በደስታ ፡ ሳቅ ፡ ሲሳይ (፪x) የለኝም ፡ ሌላ ፡ እኔ ፡ የምለዉ ይሄ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ እንኳን ፡ የማነሳው ፡ ከሰው የድስታዬ ፡ ቀኑ ፡ ባለቤት ብቻህን ፡ ታይበት ፡ ይህን ፡ ነው ፡ የምለው ተመሥገን ፣ ተመሥገን (፰x) ይገባሃል ፡ ተመሥገን (፬x) ተመሥገን (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.