Loading
Singer
አለኝ (፫x) ፡ ሚወራ ፡ ዛሬ አለኝ ፡ አለኝ ፡ ሚወራ ፡ ዛሬ እኔ ፡ አለኝ (፫x) ፡ ሚወራ ፡ ዛሬ አለኝ ፡ አለኝ ፡ ሚወራ ፡ ዛሬ አቤት ፡ አቤት ፡ ስራው አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት አዝ፦ ፍቅሩ ፡ በዛ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው ፡ መድህኔ አላስችል ፡ አለኝ ፡ ላውጣ ምላሽ ፡ ይሆን ፡ ዘንድ ፡ ላውራ ይሄ ፡ ደጉ ፡ አምላክ ፡ ደጉ ዝም ፡ አያሰኝም ፡ ፍቅሩ አትታዘቡኝ ፡ ልጩህ ፡ ተመችቶኛል ፡ ደጁ ተመችቶኛል ፡ ደጁ (፪x) ተመችቶኛል ፡ ደጁ (፪x) ተመችቶኛል (፫x) ፡ ደጁ ፡ ተመችቶኛል ተመችቶኛል (፫x) ምርጫዬ ፡ ሆኗል ፡ ከደጃፉ ፡ ስር ግራ ፡ ቀን ፡ አላይ ፡ ምቹ ፡ ነው ፡ ፍቅርህ ቀን ፡ አይቶ ፡ አይገፋም ፡ አይለወጥም በሁኔታዎች ፡ አይቀየርም አለኝ ፡ ያልኩት ፡ ሲጠፋ ፡ ተስፋ ፡ ያደረኩት ፡ ሲከዳ ኢየሱሴ ፡ ብቻውን ፡ ያለአጋዥ ፡ ረዳኝ አዝ፦ ፍቅሩ ፡ በዛ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው ፡ መድህኔ አላስችል ፡ አለኝ ፡ ላውጣ ምላሽ ፡ ይሆን ፡ ዘንድ ፡ ላውራ ይሄ ፡ ደጉ ፡ አምላክ ፡ ደጉ ዝም ፡ አያሰኝም ፡ ፍቅሩ አትታዘቡኝ ፡ ልጩህ ፡ ተመችቶኛል ፡ ደጁ ተመችቶኛል ፡ ደጁ (፪x) ተመችቶኛል ፡ ደጁ (፪x) እኔስ (፪x) ፡ ያረፍኩት ፡ የተደላደልኩት ሸክሜን ፡ በጌታ ፡ ላይ ፡ ጥዬ ፡ ቀና ፡ ብዬ ፡ የሄድኩት ቀንበሬን ፡ ሰብሮታል ፡ የምን ፡ አንገት ፡ መድፋት መንፈሱ ፡ ሲረዳኝ ፡ ሲሆንልኝ ፡ ስኬት ከእንግዲህ ፡ ዓለመለስ ፡ እሄዳለሁ ፡ ወደፊት ምርጫዬ ፡ ልክ ፡ ነው ፡ የዳንኩበት ፡ እውነት አውጥቶ ፡ አይጥልም ፡ ሁሌ ፡ ይሸከማል አያዋርድም ፡ ይልቅ ፡ ያከብራል ክፉ ፡ ተናግሮ ፡ ማስቀየም ፡ አያውቅም የፍቅር ፡ ቃሉ ፡ ተነግሮ ፡ አያልቅ በሚያባባል ፡ ቃሎቹ ፡ ውስጤን ፡ አሳርፎታል ደስ ፡ የሚያሰኘው ፡ ምክሩ ፡ ደግፎ ፡ አቁሞኛል አዝ፦ ፍቅሩ ፡ በዛ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው ፡ መድህኔ አላስችል ፡ አለኝ ፡ ላውጣ ምላሽ ፡ ይሆን ፡ ዘንድ ፡ ላውራ ይሄ ፡ ደጉ ፡ አምላክ ፡ ደጉ ዝም ፡ አያሰኝም ፡ ፍቅሩ አትታዘቡኝ ፡ ልጩህ ፡ ተመችቶኛል ፡ ደጁ ተመችቶኛል ፡ ደጁ (፪x) ተመችቶኛል ፡ ደጁ (፪x) ተመችቶኛል ፡ ደጁ (፪x) (ተመችቶኛል (፪x)) ተመችቶኛል ፡ ደጁ (፪x) (ተመችቶኛል (፪x)) ተመችቶኛል (፫x)