Loading
Singer
ትመቸኛለህ ፡ ጌታዬ ትመቸኛለህ ፡ ኢየሱስ (፪x) ከእናት ፡ ማህፀን ፡ እስከ ፡ ሽመግልና ፡ ድረስ ምተሸከም ፡ አምላክ ፡ ቃልህን ፡ ማታፈርስ ፍፁም ፡ ነው ፡ ፍቅርህ ፡ የሱስ ፡ ያለ ፡ እንከን ፡ የሆነ የኽው ፡ ተስፋ ፡ ያለው ፡ ሠው ፡ አረከኝ ፡ ህይወቴ ፡ ሰከነ (፪x) አዝ፦ ትመቸኛለህ ፡ ጌታዬ ትመቸኛለህ ፡ ኢየሱስ (፬x) በዓለም ፡ ሣለሁኝ ፡ ከአለም ፡ ተለይቼ ፡ ልኖር ከንቱ ፡ እንደሆነ ፡ አውቄ ፡ የዚህች ፡ ምድር ፡ ክብር ስደክም ፡ ስበረታ ፡ በህይወት ፡ መንገድ ፡ ላይ ክንዶች ፡ ያሣረፈኝ ፡ የደላኝ ፡ የለም ፡ ካንተ ፡ በላይ አዝ፦ ትመቸኛለህ ፡ ጌታዬ ትመቸኛለህ ፡ ኢየሱስ (፬x) ሳልወድ ፡ ወይም ፡ ሣልሮጥ ፡ ምህረትን ፡ አግኝቻለሁ ነፍሴን ፡ አርክተሀት ፡ ልዩ ፡ ሰው ፡ ሆኜአለሁ መቅበዝበዜ ፡ አሣዝኖህ ፡ ፈልገህ ፡ አግኝተኽኝ ከቶ ፡ እንዳይጠማኝ ፡ የሕይወትን ፡ ውሃ ፡ አጠጣኽኝ አዝ፦ ትመቸኛለህ ፡ ጌታዬ ትመቸኛለህ ፡ ኢየሱስ (፬x) የልቤ ፡ ፍሰሀ ፡ አምላኬና ፡ አባቴ ፡ ለኔ መቼም ፡ የማትተወኝ ፡ ማገኝህ ፡ ከጐኔ ምላሴ ፡ ሲያከብርህ ፡ በሚችለው ፡ ሁሉ የአካል ፡ ክፍሎቼ ፡ ተባብረው ፡ በደስታ ፡ ያመልካሉ አዝ፦ ትመቸኛለህ ፡ ጌታዬ ትመቸኛለህ ፡ ኢየሱስ (፰x)