Loading
Singer
ላመስግን ፡ የኔጌታ ፡ ላመስግን ላመስግን ፡ ደጋግሜ ፡ ላመስግን በጠላቴ ፡ ሰፍር ፡ እሮሮ ፡ ሲሰማ ለእኔ ፡ ግን ፡ በዛልኝ ፡ የምሥጋና ፡ ዜማ ከፊቴ ፡ የቆመው ፡ ትልቁ ፡ ተራራ ደልዳላ ፡ ሆነልኝ ፡ ስምህን ፡ ስጠራ ከፊቴ ፡ የቆመው ፡ ትልቁ ፡ ተራራ ደልዳላ ፡ ሆነልኝ ፡ ስምህን ፡ ስጠራ አዝ፦ ተማምኜ ፡ እኖራለሁ ፡ ተማምኜ (፪x) በዘላለሙ ፡ ክንድህ ፡ በቅፍህ ፡ ታምኜ አልጥልህም ፡ ብለህ ፡ በፍቅርህ ፡ ጠርተኽኝ ፡ ፀጋን ፡ አለበስከኝ በሄድኩበት ፡ ሁሉ ፡ ተከናወነልኝ ፡ ሞገስ ፡ ሆነህልኝ እንድም ፡ ነገር ፡ የለም ፡ ከኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ የኔ ፡ ነው ፡ የምለው ሁሉም ፡ ያማረልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ባንተ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ባንተ ፡ ነው አዝ፦ ተማምኜ ፡ እኖራለሁ ፡ ተማምኜ (፪x) በዘላለሙ ፡ ክንድህ ፡ በቅፍህ ፡ ታምኜ ውድቀቴን ፡ በሚሻው ፡ በጠላቴ ፡ ላይ (፪x) ከፍ ፡ ከፍ ፡ አረከኝ ፡ ክብርህ ፡ እንዲታይ (፪x) ልቤ ፡ በማዳንህ ፡ እየተደነቀ (፪x) ለታላቅነትህ ፡ ዜማን ፡ አፈለቀ (፪x) አዝ፦ ተማምኜ ፡ እኖራለሁ ፡ ተማምኜ (፪x) በዘላለሙ ፡ ክንድህ ፡ በቅፍህ ፡ ታምኜ