Loading
Singer
አዝ፦ ከሰፈር ፡ ሰፈር ውጭ ፡ ጉዋሮው ፡ ሳየቀር ከበራፍ ፡ በራፍ ከቶ ፡ አንድም ፡ ቤት ፡ ሳታልፍ አጽናኝ ፡ መንፈስ ፡ ሆይ ፡ ፈጥነህ ፡ ድረስ ፡ ለእኛ የምንወዳቸው ፡ ተለይተው ፡ ከእኛ እስከመቼ ፡ ድረስ ፡ ሆነን ፡ ሃዘንተኛ ሰውማ ፡ ዛሬም ፡ ላይ ፡ ታች ፡ ይላል አደባባዩስ ፡ መቼ ፡ ይጐላል ጨዋ ፡ ህዝብ ፡ ፈገግታ ፡ ያሳያል ልቡ ፡ ግን ፡ በሃዘን ፡ ይጋያል ወንድ ፡ ሴት ፡ ልጆቹን ፡ ያጣ ፡ ሰው እህቱን ፡ ወንድሙን ፡ ያጣ ፡ ሰው ወላጆቹን ፡ በሞት ፡ ያጣ ፡ ሰው ያጽናኝ ፡ ያለህ ፡ ይላል ፡ ሆዱን ፡ እየባሰው አዝ፦ ከሰፈር ፡ ሰፈር ውጭ ፡ ጉዋሮው ፡ ሳየቀር ከበራፍ ፡ በራፍ ከቶ ፡ አንድም ፡ ቤት ፡ ሳታልፍ አጽናኝ ፡ መንፈስ ፡ ሆይ ፡ ፈጥነህ ፡ ድረስ ፡ ለእኛ የምንወዳቸው ፡ ተለይተው ፡ ከኛ እስከመቼ ፡ ድረስ ፡ ሆነን ፡ ሃዘንተኛ ባልንጀር ፡ አብሮ ፡ አደጉን ፡ ያጣ የሥራ ፡ ባልደራባዉን ፡ ያጣ ጐረቤት ፡ ጠያቂውን ፡ ያጣ የሚያጽናናው ፡ ዛሬ ፡ ከየት ፡ ይምጣ ሞት ፡ ያልበዘበዘው ፡ ማን ፡ አለ ቤት ፡ ጓዳው ፡ ያልተመሰቃቀለ ተርታውን ፡ ከደጃፍ ፡ እደጃፍ ነጣቂው ፡ ነጠቀ ፡ ከቶ ፡ አንድም ፡ ሳያልፍ አዝ፦ ከሰፈር ፡ ሰፈር ውጭ ፡ ጉዋሮው ፡ ሳየቀር ከበራፍ ፡ በራፍ ከቶ ፡ አንድም ፡ ቤት ፡ ሳታልፍ አጽናኝ ፡ መንፈስ ፡ ሆይ ፡ ፈጥነህ ፡ ድረስ ፡ ለእኛ የምንወዳቸው ፡ ተለይተው ፡ ከኛ እስከመቼ ፡ ድረስ ፡ ሆነን ፡ ሃዘንተኛ ህጻናት ፡ ተጣለ ፡ ባዶ ፡ ቤት እናት ፡ አባት ፡ አልቀው ፡ በቅጽበት ሽማግሌዎች ፡ ጡዋሪም ፡ የላቸው ተቀጭተው ፡ ተስፋ ፡ ልጆቻቸው የፍራቻ ፡ ጥላ ፡ የሥጋት ሰንብቶአል ፡ ምድሪቱን ፡ ከዋጣት ጠዋት ፡ ያዩት ፡ በሕይወት ፡ ለማታ በነበር ፡ ይወሳል ፡ በቅጽበት ፡ በአንዳፍታ አዝ፦ ከሰፈር ፡ ሰፈር ውጭ ፡ ጉዋሮው ፡ ሳየቀር ከበራፍ ፡ በራፍ ከቶ ፡ አንድም ፡ ቤት ፡ ሳታልፍ አጽናኝ ፡ መንፈስ ፡ ሆይ ፡ ፈጥነህ ፡ ድረስ ፡ ለእኛ የምንወዳቸው ፡ ተለይተው ፡ ከኛ እስከመቼ ፡ ድረስ ፡ ሆነን ፡ ሃዘንተኛ ምናልባት ፡ ብትራራ ፡ ጌታችን የእንጨት ፡ ርብራብ ፡ ሆኗአል ፡ ቤታችን አሳር ፡ ነው ፡ ዞሮም ፡ መግባቱ አባዜው ፡ ክፍ ፡ ሆኖ ፡ የቤቱ ያልፋል ፡ ይህ ፡ የከፍ ፡ ቀን እግዚአብሔር ፡ በምረት ፡ ሲያውቀን ስብራት ፡ ይጠገንና የዓይናችን ፡ እንባ ፡ ፍፁም ፡ ይደርቅና የትናንት ፡ ወሬ ፡ ይሆንና ይሞላል ፡ ሰው ፡ በምሥጋና