Loading
Singer
አዝ:- ትልቅ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ትልቅ ፡ ትልቅ (፬x) አይችልም ፡ ምንም ፡ ማንም ፡ ከአንተ ፡ ሊልቅ (፬x) ጉልበተኛ ፡ ነው ፡ ከተባለ ፡ ምንም ፡ ነገር ተለካክቶ ፡ ነው ፡ ተወዳድሮ ፡ ከሌላው ፡ ጋር አንተ ፡ ምድርን ፡ ሰማያትን ፡ እንኳን ፡ ስጸራ የተጠቀምከው ፡ ቃልህን ፡ ነው ፡ ከአፍህ ፡ የወጣ ቃልህ ፡ ያልተፈጠረውን ፡ መፍጠር ፡ ከቻለ እንዴት ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ ነገርህ ፡ ልበል ፡ ልናገር ፡ ለአንተ አዝ:- ትልቅ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ትልቅ ፡ ትልቅ (፬x) አይችልም ፡ ምንም ፡ ማንም ፡ ከአንተ ፡ ሊልቅ (፬x) የአንተ ፡ የሆኑት ፡ ልጆችህ ፡ ከአንተ ፡ የወጡት ቃልህን ፡ በውስጥ ፡ መንፈሳቸው ፡ ስላስቀመጡት እነርሱ ፡ ሳይቀር ፡ የአንተን ፡ ቃል ፡ ሲናገሩት ስጋን ፡ ተላብሰው ፡ ሰራዊት ፡ ሆኗል ፡ ደረቅ ፡ አጥንት ዝናብ ፡ እንዳይወርድ ፡ ተከልክሎ ፡ ፀሐይ ፡ ቆማለች አይደለም ፡ አንተ ፡ ልጆችህ ፡ ናቸው ፡ ሃይለኞች አዝ:- ትልቅ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ትልቅ ፡ ትልቅ (፬x) አይችልም ፡ ምንም ፡ ማንም ፡ ከአንተ ፡ ሊልቅ (፬x) ቀላል ፡ ነው ፡ በአንተ ፡ እይታ ፡ ሳየው ይሆናል ፡ ቃል ፡ ስትወጣ ፡ ወዲያው ባለ ፡ ስልጣን ፡ ነህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ባለስልጣን ግር ፡ ግር ፡ የለም ፡ ስትናገር ፡ ሁሉ ፡ ይሰማል ይሆንልሃል ፡ እንደአፍህ ፡ አንተ ፡ እንዳልከው ስላመንኩብህ ፡ አንተን ፡ ነው ፡ የማመልከው አዝ:- ትልቅ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ትልቅ ፡ ትልቅ (፬x) አይችልም ፡ ምንም ፡ ማንም ፡ ከአንተ ፡ ሊልቅ (፬x)