Loading
Singer
የዘለዓለም ፡ መኖሪያዬ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ማረፊያዬ ታምኘብህ ፡ አላፈርኩም በምድረበዳ ፡ አልቀረሁም አዝ፦ ትልቅ ፡ ያየሁት ፡ አንተን ፡ ብቻ በምድር ፡ በሰማይ ፡ የለህ ፡ አቻ እግዚአብሔር ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ ከአማልክት ፡ ሁሉ ፡ ትለያለህ (፪x) ካየሁት ፡ ሁሉ ፡ ትበልጣለህ በክንዶችህ ፡ አየተደገፍኩ አቤት ፡ ባንተ ፡ ስንቱን ፡ አለፍኩ ማዳንህን ፡ አይቻለሁ ስለውለታህ ፡ እዝምራለሁ አዝ፦ ትልቅ ፡ ያየሁት ፡ አንተን ፡ ብቻ በምድር ፡ በሰማይ ፡ የለህ ፡ አቻ እግዚአብሔር ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ ከአማልክት ፡ ሁሉ ፡ ትለያለህ (፪x) ካየሁት ፡ ሁሉ ፡ ትበልጣለህ የዚህ ፡ ዓለም ፡ ጠቢባኖች የምድር ፡ ላይ ፡ ኃያላኖች ሁሉም ፡ ወድቀው ፡ ተረስተዋል አንተ ፡ ብቻ ፡ ያው ፡ ነህ ፡ ተከብረሃል አዝ፦ ትልቅ ፡ ያየሁት ፡ አንተን ፡ ብቻ በምድር ፡ በሰማይ ፡ የለህ ፡ አቻ እግዚአብሔር ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ ከአማልክት ፡ ሁሉ ፡ ትለያለህ (፪x) ካየሁት ፡ ሁሉ ፡ ትበልጣለህ