Loading
Singer
አዝ፦ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ብወድቅ ፡ እነሳለሁኝ በጨለማ ፡ ብቀመጥ ፡ እንኳን እግዚአብሔር ፡ ብርሃን ፡ ይሆንልኛል ስለዚህ ፡ ስለዚህ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ አይበልህ የወይኑ ፡ ፍሬ ፡ ተለቅሞ ፡ እንደቀረው ፡ ቃርሚያ ደርቄ ፡ ቆሜያለሁ ፡ እኔ ፡ ከበረከት ፡ በስቲያ የሃዘን ፡ እንጉርጉሮዬን ፡ የምሬት ፡ ለቅሶዬን በአምላኬ ፡ ፊት ፡ እለቃለሁ ፡ እንዲያያት ፡ ሕይወቴን አዝ፦ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ብወድቅ ፡ እነሳለሁኝ በጨለማ ፡ ብቀመጥ ፡ እንኳን እግዚአብሔር ፡ ብርሃን ፡ ይሆንልኛል ስለዚህ ፡ ስለዚህ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ አይበልህ በእግዚአብሔር ፡ ላይ ፡ ኃጥያትን ፡ ሰርቻለሁና ቁጣው ፡ ለቅጣቴ ፡ ሆኖ ፡ ነዶብኛልና ወደ ፡ ብርሃን ፡ እስኪያወጣኝ ፡ እታገሳለሁኝ መልሶም ፡ እስኪምረኝ ፡ ድረሰ ፡ ጠብቀዋለሁኝ አዝ፦ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ብወድቅ ፡ እነሳለሁኝ በጨለማ ፡ ብቀመጥ ፡ እንኳን እግዚአብሔር ፡ ብርሃን ፡ ይሆንልኛል ስለዚህ ፡ ስለዚህ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ አይበልህ በእኔና ፡ በአምላኬ ፡ መሃል ፡ የሚኖረውን ፡ ጉዳይ ኢየሱስ ፡ ይፈፅመዋል ፡ የመሰረቱ ፡ ድንጋይ ስለዚህ ፡ ጠላቴ ፡ ወግድ ፡ ጌታ ፡ ይገስጽህ አሁንም ፡ ቢሆን ፡ ልጁ ፡ ነኝ ፡ ተረዳ ፡ ከልብህ አዝ፦ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ብወድቅ ፡ እነሳለሁኝ በጨለማ ፡ ብቀመጥ ፡ እንኳን እግዚአብሔር ፡ ብርሃን ፡ ይሆንልኛል ስለዚህ ፡ ስለዚህ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ አይበልህ ለዘለዓለም ፡ አይቆጣም ፡ ምህረትን ፡ ይወዳል የጠላቴን ፡ ምኞት ፡ ቆርጦ ፡ ዕልልታውን፡ ያቆማል የውርደት ፡ ማቄ ፡ ተቀዶ ፡ ነጭ ፡ ልብስ ፡ ለብሼ ዳግም ፡ ዘምራለሁ ፡ ለእርሱ ፡ ክንዱን ፡ ተንተርሼ አዝ፦ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ብወድቅ ፡ እነሳለሁኝ በጨለማ ፡ ብቀመጥ ፡ እንኳን እግዚአብሔር ፡ ብርሃን ፡ ይሆንልኛል ስለዚህ ፡ ስለዚህ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ አይበልህ