Loading
Singer
አዝ፦ እባብና ፡ ጊንጡን ፡ አስረግጦናል በጠላት ፡ ኃይልም ፡ ላይ ፡ ሥልጣን ፡ ሰጥቶናል የሰላም ፡ አምላክ ፡ እግራችን ፡ ሥር ፡ ቀጥቅጦታል የሚያስቆመንም ፡ የለም ፡ ጠላት ፡ ተመቷል (፪x) የጌታን ፡ ዕቃ ፡ ጦር ፡ እንለብሳለን አይደል ፡ በደም ፡ ሥጋ ፡ መጋደላችን የዲያቢሎስን ፡ ሽንገላ ፡ ተቃውመን በአለቆች ፡ ስልጣናት ፡ ላይ ፡ እንዘምታለን የሚንበለበለውን ፡ የክፉ ፡ ፍላፃ እናጠፋዋለን ፡ አለን ፡ የእምነት ፡ ጋሻ አዝ፦ እባብና ፡ ጊንጡን ፡ አስረግጦናል በጠላት ፡ ኃይልም ፡ ላይ ፡ ሥልጣን ፡ ሰጥቶናል የሰላም ፡ አምላክ ፡ እግራችን ፡ ሥር ፡ ቀጥቅጦታል የሚያስቆመንም ፡ የለም ፡ ጠላት ፡ ተመቷል (፪x) እርሱ ፡ ከኛ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ ማን ፡ ይቃወመናል በሕይወት ፡ ጐዳና ፡ ይኸው ፡ አራምዶናል እጃችንን ፡ ይዞ ፡ መቼ ፡ ማድረስ ፡ ብቻ በድል ፡ አሻግሮናል ፡ የሞትን ፡ ዳርቻ እርሱ ፡ ኃይላችን ፡ ነው ፡ መመኪያ ፡ ክብራችን መቼም ፡ አንወድቅም ፡ አለ ፡ ከጐናችን አዝ፦ እባብና ፡ ጊንጡን ፡ አስረግጦናል በጠላት ፡ ኃይልም ፡ ላይ ፡ ሥልጣን ፡ ሰጥቶናል የሰላም ፡ አምላክ ፡ እግራችን ፡ ሥር ፡ ቀጥቅጦታል የሚያስቆመንም ፡ የለም ፡ ጠላት ፡ ተመቷል (፪x) በኃይል ፡ አይደለም ፡ በብርታት የጠላት ፡ እንዲህ ፡ መመታት በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ በእግዚአብሔር ክንዱን ፡ ተማምኖ ፡ በሚኖር (፬x)