Loading
Singer
አዝ፦ ትላንት ፡ ተብሎ ፡ ዛሬ ፡ ሊጠራ አሳልፎት ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ሁሉን ፡ በተራ አምላኬን ፡ እንዲህ ፡ በሉልኝ ፡ ሥራህ ፡ ግሩም ፡ ነው እርሱ ፡ በሰራልኝ ፡ ተዓምራት/ቀናቶች ፡ እኔ ፡ ኖራለሁ (፪x) ልዩነት ፡ አምጥቶ ፡ ሌሊቱ ለጠላቴ ፡ ሆነ ፡ ውድቀቱ ሊያጠፋኝ ፡ ነበረ ፡ ምኞቱ እንዲሁ ፡ ደከመ ፡ በከንቱ እኔማ ፡ አምልጫለሁ ፡ ወጥመዴ ፡ ተሰብሮ ጠላቴ ፡ ላይደግም ፡ አንድ ፡ ጊዜ ፡ ጥሎ እኔማ ፡ አምልጫለሁ ፡ ወጥመዴ ፡ ተሰብሮ ጠላቴ ፡ ላይደግም ፡ ከእግሬ ፡ በታች ፡ ጥሎ ይጨምራል ፡ ገና ፡ ሙሉ ፡ ቀን ፡ እስኪሆን (፪x) የአምላኬን ፡ ተዓምራት ፡ አያለሁ ፡ ማዳኑን (፪x) ለነገም ፡ ለዛሬ ፡ ምላሽ ፡ አለው ፡ ጌታ በጭራሽ ፡ አልወርድም ፡ እኔ ፡ ከአየልኝ ፡ ከፍታ አዝ፦ ትላንት ፡ ተብሎ ፡ ዛሬ ፡ ሊጠራ አሳልፎት ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ሁሉን ፡ በተራ አምላኬን ፡ እንዲህ ፡ በሉልኝ ፡ ሥራህ ፡ ግሩም ፡ ነው እርሱ ፡ በሰራልኝ ፡ ተዓምራት/ቀናቶች ፡ እኔ ፡ ኖራለሁ (፫x) ደሙ ፡ በመቃኔ ፡ በጉበኔ ፡ ላይ ፡ ነው (፪x) ቀኑ ፡ ክፉ ፡ ቢሆን ፡ ነግሬው ፡ አልፋለሁ (፪x) በሞት ፡ ጥላ ፡ ብሄድ ፡ መቼ ፡ ያስፈራኛል ሰባሪው ፡ እግዚአብሔር ፡ ከፊቴ ፡ ቀድሞ ፡ ወጥቶልኛል (፪x)