Loading
Singer
እናንተ ፡ ፡ ደካሞች ፡ ሸክማችሁ ፡ የከበዳ ፡ ፡ ሁለ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ኑ ፡ እኔም ፡ አሳርፋችኋለሁ ፡ ቀንበሬን ፡ በላያችሁ ፡ ተሸከሙ ፡ ከእኔም ፡ ተማሩ እኔ ፡ የዋህ ፡ በልቤም ፡ ትሁት ፡ ነኝና ፡ ለነፍሳችሁም ፡ እረፍት ፡ ታገኛላችሁ ቀንበሬ ፡ ልዝብ ፡ ሸክሜም ፡ ቀሊል ፡ነውና ፡ (የማቲዎስ ፡ ወንጌል ፡ ምህራፍ ፡ ፲፩ ፡ ፳፮ ፴) ያላሸከመከኝን ፡ እንዳልሸከም ፡ ከብዶኝ ፡ አንገዳግኝ ፡ እንዳልደክም ያላሳየኸኝን ፡ አይቼ ፡ እንዳልቆም ፡ ግራ ፡ ተጋብቼ ያልሰጠኸኝንም ፡ ወስጄ ፡ እንዳልቀር ፡ ኋላ ፡ ባዶ ፡ እጄን የላደረከኝንም ፡ ሆኜ ፡ እንዳልቀል ፡ በአንተ ፡ ተመዝኜ ፡ ትሁቱ ፡ ከአንተ ፡ መማር ፡ እፈልጋለሁ ፡ ታዘኸውን ፡ እግዚአብሔርን ፡ ደስ ፡ እንዳስኘኸው ፡ ትሁቱ ፡ ከአንተ ፡ መማር ፡ እፈልጋለሁ ፡ ታዘኸውን ፡ እግዚአብሔርን ፡ ደስ ፡ እንዳስኘኸው ፡ አስተምረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ መንገድህን ፡ ፡ አንተን ፡ ተክትዬ ፡ መራመድን ፡ እኔ ፡ ትሁት ፡ ነኝ ፡ ከኔ ፡ ተማሩ ፡ እንዳልክ ፡ እሺ ፡ አስተምረኝ ፡ አንተ ፡ እንደፈልክ ስታዘኝ ፡ ሳልታዘዝህ ፡ ቀርቼ እንዳልገኝ ፡ ለጠላቴ ፡ ተመችቼ ስጠራኝ ፡ ድምጽህን ፡ ሳላውቀው ፡ ለይቼ እንዳልጠፋ ፡ በክፉው ፡ እጅ ፡ ተነድቼ ባስቀመጥከኝ ፡ በስፍራዬ ፡ ሳልቀመጥ እንዳታጣኝ ፡ በቦታዬ ፡ ስትገለጥ በሰጠኸኝ ፡ በመክሊቴ ፡ ሳላፈራ እንዳትመጣብኝ ፡ የአንተን ፡ ስራ ፡ ሳልሰራ በፈቃዴ ፡ በስሜቴ ፡ እየኖርኩኝ ፡ ጌታ ፡ እንዳልስት ፡ የአንተ ፡ ፈቃድ ፡ ነው ፡ እያልኩኝ የቆምኩኝ ፡ መስሎኝ ፡ ሳልቆም ፡ የቀረሁ ፡ እንዳልሆን እንዳልወድቅ ፡ ኋላ ፡ ልጠንቀቅ ፡ አሁን አለሁ ፡ እያልኩኝ ፡ በቤትህም ፡ እኖራለሁ ውጭ ፡ እንዳልሆን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እፈራለሁ ፡ ዛሬ ፡ ብገኝ ፡ በአንተ ፡ ወደ ፡ አምላክ ፡ ቀርቤ እንዳልዘነጋው ፡ በአንተ ፡ መሆኑን ፡ መታሰቤ ፡ ትሁት ፡ የአንተን ፡ ቀንበር ፡ እሸከማለሁ ፡ ልዝብ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ማረስ ፡ እቻላለሁ ፡ ትሁት ፡ የአንተን ፡ ቀንበር ፡ እሸከማለሁ ፡ ልዝብ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ማረስ ፡ እቻላለሁ ፡ አንተን ፡ ተክትዬ ፡ መራመድን ፡ እኔ ፡ ትሁት ፡ ነኝ ፡ ከኔ ፡ ተማሩ ፡ እንዳልክ ፡ እሺ ፡ አስተመረኝ ፡ አንተ ፡ እንደፈልክ አንተ ፡ ምራኝ ፡ አንተው ፡ መዳን ፡ እንደሆንከኝ ፍጻሜዬን ፡ አንተው ፡ አሳምርልኝ እንዳረከኝ ፡ ብቻ ፡ እንዳልከኝ ፡ አድርገኝ ሁልጊዜ ፡ በአንተ ፡ ውስጥ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰውረኝ አንተ ፡ እዘዘኝ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ በኔ ፡ ስራ እኔም ፡ ከፈቃድህ ፡ ልስማማ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ይስማማኛል ፡ ልዝብ ፡ ነው ፡ ቀንበርህ አሸከመኝ ፡ ቀሊል ፡ ነው ፡ የአንተ ፡ ሸክምህ ፡ ትሁቱ ፡ የአንተን ፡ ሸክም ፡ እሸከማለሁ ፡ ቀሊል ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ መሄን ፡ እችላለሁ ፡ ትሁት ፡ የአንተን ፡ ሸክም ፡ እሸከማለሁ ፡ ቀሊል ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ማሄድ ፡ እችላለሁ ፡ አስተምረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ መንገድህን ፡ ፡ አንተን ፡ ተክትዬ ፡ መራመድን ፡ እኔ ፡ ትሁት ፡ ነኝ ፡ ከኔ ፡ ተማሩ ፡ እንዳልክ ፡ እሺ ፡ አስተመረኝ ፡ አንተ ፡ እንደፈልክ አያስኬድም ፡ ሌላው ፡ ፈጽሞ ፡ አይመችም የሚያስቆም ፡ ነው ፡ ወደፊት ፡ አያራምድም አይስማማም ፡ ፍፁም ፡ አይሰጥም ፡ ደስታ ባዶነት ፡ ነው ፡ ከንቱ ፡ ያለ ፡ አንተ ፡ ጌታ ማትረፍ ፡ የለም ፡ መክሰር ፡ ነው ፡ በጉዞዬ የለአንተ ፡ ግቡ ፡ አይደርሥም ፡ አላማዬ ፡ እንተ ፡ እንዳልክ ፡ ከአንተ ፡ መማርን ፡ መርጣለሁ ስታደርገው ፡ እያየሁ ፡ አከብርሃለሁ ፡ ትሁቱ ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ እሺ ፡ እላላሁ ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ አርፌ ፡ መጉዋዝን ፡ እሻለሁ ፡ ትሁቱ ፡ የአንተን ፡ ቀንበር ፡ እሸከማለሁ ፡ ልዝህብ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ማረስ ፡ እችላለሁ ፡ ትሁቱ ፡ የአንተን ፡ ሸክም ፡ እሸከማለሁ ፡ ቀሊል ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ መሄድ ፡ እችላለሁ