Loading
Singer
አዝ፦ ትህትና ፡ ሊያስተምረኝ ፡ ወዶ እግር ፡ አጠበ ፡ ባርያውን ፡ ወርዶ እራሱን ፡ አዋርዶ (፪x) ደቀ ፡ መዛሙርቱ ፡ አግራቸው ፡ ቆሸሸ አደፈ ፡ ጐደፈ ፡ ፍፁም ፡ ተበላሸ ሁሉን ፡ የፈጠረ ፡ ሰውን ፡ የወደደ ጭቃውን ፡ ሊያስወግድ ፡ ወደታች ፡ ወረደ አዝ፦ ትህትና ፡ ሊያስተምረኝ ፡ ወዶ እግር ፡ አጠበ ፡ ባርያውን ፡ ወርዶ እራሱን ፡ አዋርዶ (፪x) እርሱ ፡ ያላጠበው ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ አይኖርም አይቆርስም ፡ ከአምላክ ፡ ጋራ ፡ አንድነት ፡ የለውም ጴጥሮስ ፡ ይህን ፡ አይቶ ፡ ሰውነቴን ፡ ደግሞ እጠበኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አለውም ፡ ተማጽኖ አዝ፦ ትህትና ፡ ሊያስተምረኝ ፡ ወዶ እግር ፡ አጠበ ፡ ባርያውን ፡ ወርዶ እራሱን ፡ አዋርዶ (፪x) በሚደነቅ ፡ ብርሃን ፡ የሚኖር ፡ ፈጣሪ አልፋና ፡ ኦሜጋ ፡ የፍጥረታት ፡ ሰሪ ማበሻ ፡ ጨርቅ ፡ ወስዶ ፡ እግር ፡ ሊያጥብ ፡ ወረደ ዝቅ ፡ አደረገ ፡ እራሱን ፡ ለሰው ፡ አዋረደ አዝ፦ ትህትና ፡ ሊያስተምረኝ ፡ ወዶ እግር ፡ አጠበ ፡ ባርያውን ፡ ወርዶ እራሱን ፡ አዋርዶ (፪x) የሁሉ ፡ ማሰሪያ ፡ አላማ ፡ ያለው ፡ ነው ጌታ ፡ ይህን ፡ አድርጓል ፡ እኔስ ፡ እንደምነው የወንድሜን ፡ እግር ፡ እስካጥብ ፡ ዝልቅ ፡ ካልኩ እውነትም ፡ ኢየሱስን ፡ በእርግጥ ፡ ተከተልኩ አዝ፦ ትህትና ፡ ሊያስተምረኝ ፡ ወዶ እግር ፡ አጠበ ፡ ባርያውን ፡ ወርዶ እራሱን ፡ አዋርዶ (፪x) ባሪያ ፡ ከሚያኖረው ፡ አይበልጥም ፡ አላቸው መልዕክተኛም ፡ አይበጅ ፡ ይልቁን ፡ ከላከው እንግዲህ ፡ ጌታችሁ ፡ እኔ ፡ ይህን ፡ ስፈጽም አድርጉት ፡ ለሁሉም ፡ ዛሬ ፡ ሁኑ ፡ እናንተም አዝ፦ ትህትና ፡ ሊያስተምረኝ ፡ ወዶ እግር ፡ አጠበ ፡ ባርያውን ፡ ወርዶ እራሱን ፡ አዋርዶ (፪x)