Loading
Singer
አዝ፦ እውነት ፡ ተገልጦልኛልና ፡ ወደኋላ ፡ አልመለስም (፪x) በአለማወቅ ፡ የኖርኩባቸው ፡ ዘመናቶቼ ዳግመኛ ፡ እንዳላያቸው ፡ በአምላኬ ፡ እረሳኋቸው (፪x) ጸያፍ ፡ ነበረ ፡ ምግባሬ ፡ በደሌም ፡ በዝቶ ፡ ነውሬ እርሱ ፡ ባይረዳኝ ፡ ረድኤቴ ፡ አክትሞ ፡ ነበር ፡ ሕይወቴ ከገደል ፡ አፋፍ ፡ መለሰኝ ፡ የሞትን ፡ ጽዋ ፡ ሳልቀምሰው እራርቶልኛል ፡ በፍቅሩ ፡ ምሥጋና ፡ ክብር ፡ ይድረሰው ለአምላኬና ፡ ለሥሙ ፡ ክብር ስዘምር ፡ ውዬ ፡ ስዘምር ፡ ባድር ለአምላኬማ ፡ አይገልጽልኝም የውስጥ ፡ የልቤን ፡ ያለኝን ፡ ፍቅር (፪x) አዝ፦ እውነት ፡ ተገልጦልኛልና ፡ ወደኋላ ፡ አልመለስም (፪x) በአለማወቅ ፡ የኖርኩባቸው ፡ ዘመናቶቼ ዳግመኛ ፡ እንዳላያቸው ፡ በአምላኬ ፡ እረሳኋቸው (፪x) የጽድቅን ፡ መንገድ ፡ ስልሳውቀው ጉዙው ፡ አድክሞኝ ፡ ዝያለሁ እረፍት ፡ የሌለው ፡ እርካታ ውሸት ፡ ነው ፡ የዓለም ፡ ደስታ መውጣት ፡ መውረዱ ፡ መልፋቱ እርባን ፡ አቢስ ፡ ነው ፡ ሁሉ ፡ ከንቱ ዓይኖቹ ፡ በርተው ፡ ላየው ፡ ሰው የኢየሱስ ፡ መሆን ፡ መታደል ፡ ነው ለአምላኬና ፡ ለሥሙ ፡ ክብር ስዘምር ፡ ውዬ ፡ ስዘምር ፡ ባድር ለአምላኬማ ፡ አይገልጽልኝም የውስጥ ፡ የልቤን ፡ ያለኝን ፡ ፍቅር (፪x)