Loading
Singer
አዝ:- ተገልብጧል ፡ ታሪክ ፡ ሌላ ፡ ነገር ፡ ተፈጥሯል ንጉሡ ፡ እግዚአብሔር ፡ ምስኪኑን ፡ እረድቶታል ተዓምር ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ይሄ ፡ ሰው ፡ ቆመ ፡ በእግሩ ተወራ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ በአምላኩ ፡ እርሱ ፡ መክበሩ (፪x) ይሄው ፡ ተራ ፡ ደርሶት ፡ ምሥጋናን ፡ ሊሰዋለት ወጣ ፡ አደባባይ ፡ ላይ ፡ ማቁ ፡ ተቀዳዶለት አከናውኖለታል ፡ ደስታው ፡ ወሰን ፡ ልክ ፡ የለው ይሄን ፡ ችግረኛ ፡ እግዚአብሔር ፡ አሰበው አዝ:- ተገልብጧል ፡ ታሪክ ፡ ሌላ ፡ ነገር ፡ ተፈጥሯል ንጉሡ ፡ እግዚአብሔር ፡ ምስኪኑን ፡ እረድቶታል ተዓምር ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ይሄ ፡ ሰው ፡ ቆመ ፡ በእግሩ ተወራ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ በአምላኩ ፡ እርሱ ፡ መክበሩ (፪x) ተባርኮለት ፡ ጓዳው ፡ መከራውን ፡ እረሳው ታምኖበታልና ፡ ጌታው ፡ በብዙ ፡ እረዳው ምርኮው ፡ ተመለሰ ፡ የአጥፍ ፡ እጥፍ ፡ ሆነለት ካሰው ፡ ያጣውን ፡ ሁሉ ፡ እየነዳ ፡ አመጣለት አዝ:- ተገልብጧል ፡ ታሪክ ፡ ሌላ ፡ ነገር ፡ ተፈጥሯል ንጉሡ ፡ እግዚአብሔር ፡ ምስኪኑን ፡ እረድቶታል ተዓምር ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ይሄ ፡ ሰው ፡ ቆመ ፡ በእግሩ ተወራ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ በአምላኩ ፡ እርሱ ፡ መክበሩ (፪x) ተራራ ፡ ላይ ፡ አወጣው ፡ የናቁት ፡ ሁሉ ፡ እንዲያዩት በምላስ ፡ አለንጋ ፡ ሌት ፡ ተቀን ፡ የገረፉት ሲሸላልመው ፡ አዪ ፡ በሞገስ ፡ ሲቀባባው ውስጡንም ፡ ላዩንም ፡ እንደ ፡ አበባ ፡ ሲያፈካው አዝ:- ተገልብጧል ፡ ታሪክ ፡ ሌላ ፡ ነገር ፡ ተፈጥሯል ንጉሡ ፡ እግዚአብሔር ፡ ምስኪኑን ፡ እረድቶታል ተዓምር ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ይሄ ፡ ሰው ፡ ቆመ ፡ በእግሩ ተወራ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ በአምላኩ ፡ እርሱ ፡ መክበሩ (፪x) ቀና ፡ አለ ፡ ከአንገቱ ፡ ማቀርቀሩ ፡ ቀረና ያስተከዘው ፡ ኑሮ ፡ ድንገት ፡ ተቀየረና እነዛም ፡ ዘባቾች ፡ ሲረቱ ፡ አሉ ፡ ተደንቀው የረዳህን ፡ አምላክ ፡ እርሱን ፡ ነው ፡ የምናመልከው አዝ:- ተገልብጧል ፡ ታሪክ ፡ ሌላ ፡ ነገር ፡ ተፈጥሯል ንጉሡ ፡ እግዚአብሔር ፡ ምስኪኑን ፡ እረድቶታል ተዓምር ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ይሄ ፡ ሰው ፡ ቆመ ፡ በእግሩ ተወራ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ በአምላኩ ፡ እርሱ ፡ መክበሩ (፪x) ተአምር ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ይሄ ፡ ሰው ፡ ቆመ ፡ በእግሩ ተወራ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ በአምላኩ ፡ እርሱ ፡ መክበሩ (፫x)