Loading
Singer
አመጻዬ ፡ ወደ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ወሰደችኝ ውኃ ፡ በሌለው ፡ በረሃ ፡ አንከራተተችኝ ለውድቀቴ ፡ እውቀት ፡ ትዕቢትን ፡ አስተማረችኝ ጥማት ፡ ሲያቃጥለኝ ፣ እልህ ፡ ሲታገለኝ እውነት ፡ ስትወርሰኝ ፣ ጥበብ ፡ ስትገስጸኝ መንፈሱ ፡ ሲረታኝ ፣ ጌታን ፡ አገነሁት አዝ፦ ጠቢብ ፡ በጥበቡ ፡ አይመካ ኃያልም ፡ በኃይሉ ፡ አይመካ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጽድቅንና ፡ ፍርድን በምድር ፡ ላይ ፡ ማድረጉን ፡ ያወቀ በጌታ ፡ ይመካ (፪x) ሰማያዊ ፡ ጥበብ ፡ ዓይንን ፡ ትከፍታለች ለሰነፎች ፡ ብልሃትን ፡ ታስተምራለች ከምዝምዝ ፡ ወርቅና ፡ ከቀይ ፡ ዕንቁ ፡ ትበልጣለች አጥብቀህ ፡ ብትሻት ፡ ብትፈላልጋት ድምጽህን ፡ አንስተህ ፡ ጥበብን ፡ ብጠራት ያን ፡ ጊዜ ፡ ታውቃለህ ፡ እግዚአብሔርን ፡ መፍራት አዝ፦ ጠቢብ ፡ በጥበቡ ፡ አይመካ ኃያልም ፡ በኃይሉ ፡ አይመካ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጽድቅንና ፡ ፍርድን በምድር ፡ ላይ ፡ ማድረጉን ፡ ያወቀ በጌታ ፡ ይመካ (፪x) የዚህች ፡ ዓለም ፡ መርማሪ ፡ ወዴት ፡ አለ የዘመናትን ፡ ጥያቄ ፡ ያቃለለ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሊቁ ፡ ለእኛ ፡ የተሰቀለ ከበረሃው ፡ መሃል ፡ ሕይወት ፡ ያፈለቀ የሰይጣንን ፡ ስልጣን ፡ መትቶ ፡ ያደቀቀ ለእርሱ ፡ ስንሸነፍ ፡ ጥያቄው ፡ አለቀ አዝ፦ ጠቢብ ፡ በጥበቡ ፡ አይመካ ኃያልም ፡ በኃይሉ ፡ አይመካ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጽድቅንና ፡ ፍርድን በምድር ፡ ላይ ፡ ማድረጉን ፡ ያወቀ በጌታ ፡ ይመካ (፪x)