Loading
Singer
ጥበብን ፡ የሚሰጥ ፡ ጥበበኛ የሕይወት ፡ ውኃ ፡ ወንዝ ፡ የእኔ ፡ መገኛ እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ የእኔ ፡ ነው ኧረ/እስቲ ፡ ማነው ፡ ከእኔ ፡ ሚለየው (፪x) ልጅ ፡ ቢወለድ ፡ ከባለጠጋ ይካፈላል ፡ ከአባቱ ፡ ጋር ሃብቱ ፡ ሁሉም ፡ ቅርሱ ፡ የእርሱ ፡ ነው ግን ፡ የሚያልፍ ፡ ጊዜያዊ ፡ ነው የእኔስ ፡ አባት ፡ ከሁሉ ፡ የላቀ ሁሉን ፡ ገዢ ፡ በዓለም ፡ የታወቀ እኮራለሁ ፡ ልጁ ፡ በመሆኔ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ አባቴ ፡ ለእኔ ኃጢአት ፡ አልስራ ፡ እንጂ ፡ የማያከብረውን ሌላ ፡ ምን ፡ ይኖራል ፡ እኔና ፡ እርሱን ፡ ሚለየን በፀጋው ፡ በርትቼ ፡ እኖርለታለሁ እንደ ፡ ሚያግዘኝ ፡ ጌታን ፡ አምነዋለሁ አባ ፡ አባ ፡ ብዬ ፡ ስለው አቤት ፡ ሚለኝ ፡ የቅርቤ ፡ ነው ሚጠብቀኝ ፡ እንደ ፡ ዓይኑ ፡ ብሌን ማን ፡ ሊወስደው ፡ ከእኔ ፡ ጌታዬን የእኔስ ፡ አባት ፡ ከሁሉ ፡ የላቀ ሁሉን ፡ ገዢ ፡ በዓለም ፡ የታወቀ እኮራለሁ ፡ ልጁ ፡ በመሆኔ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ አባቴ ፡ ለእኔ ኃጢአት ፡ አልስራ ፡ እንጂ ፡ የማያከብረውን ሌላ ፡ ምን ፡ ይኖራል ፡ እኔና ፡ እርሱን ፡ ሚለየን በፀጋው ፡ በርትቼ ፡ እኖርለታለሁ እንደ ፡ ሚያግዘኝ ፡ ጌታን ፡ አምነዋለሁ