Loading
Singer
ሰው ፡ ሰውን ፡ ይወዳል ፡ ይቀርባል ፡ ለጥቅሙ ቢጤውን ፡ ፈልጐ ፡ እንዳሳቡ እኔን ፡ ግን ፡ የገረመኝ ፡ የደነቀኝ እ/ር ፡ ወዶኛል ፡ እንዲሁ ፡ እንዲሁ (፪x) ተሰማ ፡ ምስራቹ ፡ ሜዳ ፡ ባደሩ ፡ በእረኞቹ ወንጌሉ ፡ ተሰበከ ፡ ባልተማሩ ፡ ዓሣ ፡ አጥማጆች ቢሉትም ፡ ግብዞቹ ፡ ያሃጢያተኞች ፡ ዋና ፡ ወዳጅ እልቀረም ፡ ሳይማርከው ፡ ያንን ፡ ባዩን ፡ ያን ፡ አሳዳጅ ጥበበኞችን ፡ ሊያሳፍር ፡ ያለምን ፡ ደካሞች ፡ መረጠ የከበሩትን ፡ ሊያሳፍር ፡ ምናምንቴዉን ፡ አከበረ ይሄው ፡ የዓለም ፡ ቤዛ ፡ ያለም ፡ ንጉስ ፡ ቤቴ ፡ ገባ ከእኔ ፡ ጋር ፡ እራት ፡ ሊቆርስ ፡ በረከቱን ፡ ሊያፈስስ ደካሞችን ፡ ሲጠራ ፡ ለእኔም ፡ ደርሶኛል ፡ ጥሪው ፈልጐ ፡ ከመረጠ ፡ ለምን ፡ አይባል ፡ ምርጫው ጥበበኞችን ፡ ሊያሳፍር ፡ ያለምን ፡ ደካሞች ፡ መረጠ የከበሩትን ፡ ሊያሳፍር ፡ ምናምንቴዉን ፡ አከበረ ጌታን ፡ ሳገለግል ፡ በምን ፡ ጥሩ ፡ ጐኔ እንዲህ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ታሪክ ፡ የለኝ ፡ እኔ መረጠኝ ፡ ወደደኝ ፡ ፈለገኝ ፡ መድህኔ እንዲሁ ፡ እንዲሁ ፡ ከነምኔ ፡ ከነምኔ (፫x)