Loading
Singer
ስለደህንነቴ/ስለመጠራቴ ፡ ዘምሬ ፡ ሳልጨርስ ወደ ፡ ሌላ ፡ አላልፍም ፡ ጐርፍ ፡ . (1) . ፡ ቢደርስ በክብር ፡ ወደላይ ፡ ያረገውን ፡ ንጉሥ ደስታዬ ፡ ልክ ፡ የለው ፡ እርሱን ፡ ሳሞጋግስ (፪x) እርሱን ፡ ሳሞጋግስ (፪x) ፣ ጌታን ፡ ሳሞጋግስ (፪x) እርሱን ፡ ሳሞጋግስ (፪x) ፣ ጌታን ፡ ሳሞጋግስ (፪x) በምሥጋና ፡ ልቁም ፡ ፊቱ ፡ በደስታ (፪x) እግሮቼም ፡ ጸኑልኝ ፡ ቆምኩኝ ፡ በከፍታ (፪x) መዳኔ ፡ ማምለጤ ፡ ኦሆሆ ፡ ትንግርት ፡ ሆኖብኛል (፪x) በሚወደው ፡ ልጁ ፡ እግዚአብሔር/ጌታዬ ፡ ታርቆኛል (፪x) አዝ፦ ተዓምር ፡ ነው ፡ መዳኔ ፡ ለእኔ ቆሜ ፡ ፊትህ ፡ መዘመሬ ወደኸኝ ፡ ድኛለሁና ተቀበል ፡ ከእኔ ፡ ምሥጋና ከእኔ ፡ ምሥጋና ፡ ጌታ ፤ ከእኔ ፡ ምሥጋና ከእኔ ፡ አምልኮ ፤ ከእኔ ፡ አምልኮ ከእኔ ፡ ዝማሬ ፤ ከእኔ ፡ ዝማሬ ከእኔ ፡ ምሥጋና ፡ ጌታ ፤ ከእኔ ፡ ምሥጋና እኔስ ፡ ከነገሬ ፡ ድኜ ፡ መዘመሬ (፪x) ከሁሉም ፡ ሚበልጠው ፡ መዳኔ ፡ ነው ፡ ክብሬ (፪x) ሰው ፡ ሆነህ ፡ ከሰማይ ፡ የወረድከው ፡ ጌታ (፪x) ሁሌ ፡ ላመስግንህ ፡ አለብኝ ፡ ውለታ (፪x) አዝ፦ ተዓምር ፡ ነው ፡ መዳኔ ፡ ለእኔ ቆሜ ፡ ፊትህ ፡ መዘመሬ ወደኸኝ ፡ ድኛለሁና ተቀበል ፡ ከእኔ ፡ ምሥጋና ከእኔ ፡ ምሥጋና ፡ ጌታ ፤ ከእኔ ፡ ምሥጋና ከእኔ ፡ አምልኮ ፤ ከእኔ ፡ አምልኮ ከእኔ ፡ ዝማሬ ፤ ከእኔ ፡ ዝማሬ ከእኔ ፡ ምሥጋና ፡ ጌታ ፤ ከእኔ ፡ ምሥጋና