Loading
Singer
ታሪኬ ፡ የጀመረው (፫x) በመስቀሉ ፡ ሥር ፡ ነው (፪x) የተነሳበትን ፡ የማያውቅ ፡ የሚደርስበትን ፡ አያውቅም የተወለድኩ ፡ ቀን ፡ ታሪኬ ፡ እንደተጀመረ ፡ እንኳን ፡ ባውቅም ከዚህ ፡ ዕውቀት ፡ ልኩ ፡ ያለፈ ፡ ሌላ ፡ ዕውቀት ፡ ተገልጦልኛል የታሪኬ ፡ ጅምር ፡ መነሻው ፡ ከመስቀሉ ፡ ግርጌ ፡ ሆኖኛል ያወኩት ፡ ቀን ፡ አምላኬን ፡ ጌታዬ ስቀበለው ፡ እንደግል ፡ አዳኜ ስመዘገብ ፡ በሕይወት ፡ መዝገብ ፡ ላይ ጀማመረ ፡ ታሪኬ ፡ እዚያ ፡ ላይ (፪x) ታሪኬ ፡ የጀመረው (፫x) በመስቀሉ ፡ ሥር ፡ ነው (፪x) ሰው ፡ ሞቶ ፡ ሲሸኝ ፡ ወደ ፡ ቀብር ፡ ሁሉም ፡ አልቅሶ ፡ ይሸኘዋል ቀብረው ፡ ሲመለሱ ፡ ታሪኩን ፡ በቃ ፡ ሁሉም ፡ ይዘነጉታል የእኔ ፡ ግን ፡ ከዚህ ፡ የተለየ ፡ ነው ፡ ታሪኬ ፡ እዛ ፡ ላይ ፡ አያበቃም ወደ ፡ ዘለዓለማዊው ፡ ሃገሬ ፡ ጭራሽ ፡ ወደ ፡ ሌላ ፡ ይሻገራል ነፍሴ ፡ ከሥጋዬ ፡ ስትለያይ ወደ ፡ ጌታዋ ፡ ስትሄድ ፡ ወደ ፡ ላይ ሌላ ፡ ታሪክ ፡ ደግሞ ፡ ጀምራለሁ ወደ ፡ አዳነኝ ፡ ጌታ ፡ እሄዳለሁ (፪x) ታሪኬ ፡ የሚቀጥለው (፫x) ከሞት ፡ ባሻገር ፡ ነው (፪x)