Loading
Singer
አዝ:- ታሪኬ ፡ ተለውጧል ፡ ሌላ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ እውነተኛውን ፡ አዳኝ ፡ አግኝቼ ፡ አርፌያለሁ (፪x) መረጠኝ ፡ ሳልመርጠው ፡ ፈለገኝ ፡ ሳልፈልገው ከዜምናት ፡ በፊት ፡ ያሰበውን ፡ አደረገው ማን ፡ ሊከለክለው ፡ ነው ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ ሊቃወመው ኃጢአተኛውን ፡ ወዶት ፡ በደሙ ፡ ከቀደሰው አዝ:- ታሪኬ ፡ ተለውጧል ፡ ሌላ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ እውነተኛውን ፡ አዳኝ ፡ አግኝቼ ፡ አርፌያለሁ (፪x) የሞት ፡ መውጊያው ፡ ተሰብሮ ፡ ስልጣን ፡ አጣ ፡ በእኔ ፡ ላይ አልቻለም ፡ ሊያስቀረኝ ፡ ከመንግሥተ ፡ ሰማይ አልመለስባትም ፡ ወደ ፡ እዚያች ፡ መራራ ፡ ዓለም ከእንግዲህ ፡ የኢየሱስ ፡ ነኝ ፡ እስከ ፡ ዘለዓለም አዝ:- ታሪኬ ፡ ተለውጧል ፡ ሌላ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ እውነተኛውን ፡ አዳኝ ፡ አግኝቼ ፡ አርፌያለሁ (፪x) ሳላውቀው ፡ ያሰረኝን ፡ የገዛኝን ፡ ረገጥኩት ክፉ ፡ ባለጋራዬን ፡ አለሁ ፡ እየተበቀልኩት ኃይል ፡ አለው ፡ መንፈስ ፡ አለኝ ፡ ባዶዬን ፡ አይደለሁም ደፍሬው ፡ እዋጋዋለሁኝ ፡ ጠላቴን ፡ አልሸሸውም አዝ:- ታሪኬ ፡ ተለውጧል ፡ ሌላ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ እውነተኛውን ፡ አዳኝ ፡ አግኝቼ ፡ አርፌያለሁ (፪x) ለክፋት ፡ የፈጠኑት ፡ እግሮቼ ፡ ዛሬ ፡ ሰክነው ማዳኑን ፡ ለመናገር ፡ ለወንጌል ፡ እየሮጡ ፡ ነው የታሰሩ ፡ እንዲፈቱ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ እንዲለቀቁ ከጨለማ ፡ ዓለም ፡ ወጥተው ፡ እንደ ፡ ፀሐይ ፡ እንዲደምቁ አዝ:- ታሪኬ ፡ ተለውጧል ፡ ሌላ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ እውነተኛውን ፡ አዳኝ ፡ አግኝቼ ፡ አርፌያለሁ (፪x)