Loading
Singer
ታማኝ ፡ ሰው ፡ ጠፋ ፡ በአገሩ ታማኝ ፡ ሰው ፡ ጠፋ ፡ በምድሩ ሰዎች ፡ አላገኙም ፡ ቢዞሩ ፡ ቢዞሩ በፈረሥም ፡ ጠፋ ፡ እንኳንስ ፡ ሰው ፡ በእግሩ ታማኝ ፡ ግን ፡ በሰማይ ፡ አለ ፡ በመንበሩ በእርጅናዬ ፡ ዘመን ፡ አንድ ፡ እውነት ፡ አገኘሁ አደራ ፡ ማይበላ ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው ብዙ ፡ ወሰደብኝ ፡ ሚስጢሩ ፡ ሳይገባኝ ይሄ ፡ ሰው ፡ ማመኔ ፡ ደህና ፡ አድርጐ ፡ ጐዳኝ የዘመናት ፡ ጥቅልል ፡ የምድር ፡ እና ፡ ሰማይ የጌታን ፡ መመለስ ፡ በሁለት ፡ ዐይኖቸ ፡ ላይ ያወኩት ፡ ዛሬ ፡ ስአቱ ፡ መድረሱን ያበላሁት ፡ ወዳጂ ፡ ሲያፋጭብኝ ፡ ጥርሱን ዘመን ፡ ተለዋውጧል (፪x) በኩርናን ፡ በእንጐቻ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ለውጧል ጨዋነትና ፡ ክበር ፡ ውህ ፡ ፈሰሰበት የቃል ፡ አምነት ፡ ቀርቷል ፡ ፊርማ ፡ ከሌለበት ታማኝ ፡ ሰው ፡ ጠፋ ፡ በአገሩ ታማኝ ፡ ሰው ፡ ጠፋ ፡ በምድሩ ሰዎች ፡ አላገኙም ፡ ቢዞሩ ፡ ቢዞሩ በፈረሥም ፡ ጠፋ ፡ እንኳንስ ፡ ሰው ፡ በእግሩ ታማኝ ፡ ግን ፡ በሰማይ ፡ አለ ፡ በመንበሩ እወየው ፡ ጯዋነት ፡ ሰፈር ፡ ጥሎ ፡ ሄዷል ወገን ፡ በወገኑ ፡ ያልፍርሃት ፡ ነግዷል ያስቀመጡት ፡ እቃ ፡ አይገኝም ፡ ዳግም ሁሉ ፡ ቃል ፡ አጥፊ ፡ መሃላ ፡ ቢያደርግም ወንድሞቹ ፡ ሸጡት ፡ ዮሴፍን ፡ ለእንጀራ ማዕድ ፡ የተጋሩት ፡ ሆኑት ፡ ባላጋራ የጥንት ፡ ታሪክ ፡ ነው ፡ ዛሬ ፡ በዚህ ፡ የለም ብዬ ፡ ነበር ፡ ኋላ ፡ በራሴ ፡ ሊፈጸም ዘመን ፡ ተለዋውጧል (፪x) በኩርናን ፡ በእንጐቻ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ለውጧል ጨዋነትና ፡ ክብር ፡ ውህ ፡ ፈሰሰበት የቃል ፡ እምነት ፡ ቀርቷል ፡ ፊርማ ፡ ከሌለበት