Loading
Singer
፡ ፡ ያዝ ፡ ለቀቅ ፡ ሔድ ፡ መጣ ፡ ገባ ፡ ወጣ ሕይወት ፡ ትርጉም ፡ ሲያጣ ወይ ፡ ከየሱስ ፡ ወይ ፡ ከዓለም ፡ ምረጥ ፡ እንጂ ሦስት ፡ መንገድ ፡ የለም እንጀራ ፡ ለመብላት ፡ ሺ ፡ ተሰበሰበ መስቀል ፡ ለመሸከም ፡ አንድም ፡ አልቀረበ ተዓምር ፡ ለማየት ፡ እልፍ ፡ ሰው ፡ ቢንጋጋ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው፡ ፡ በጦር ፡ የተወጋ ፡ ፡ :አዝ፦ ያዝ ፡ ለቀቅ በየመንገድ ፡ ወራጅ ፡ ሞልቷል ፡ ተሳፋሪ ከጠጣ ፡ በኋላ ፡ ወጭቱን ፡ ሰባሪ ትላንትን ፡ አትርሳ ፡ አትሁን ፡ ውለታ ፡ ቢስ ገባ ፡ ወጣ ፡ አትበል ፡ ጸንተህ ፡ ቁም ፡ በየሱስ ፡ ፡ :አዝ፦ ያዝ ፡ ለቀቅ ድንኳን ፡ አስከሚወርድ ፡ ድግስ ፡ ተጠናቆ ስደት ፡ አስኪመጣ ፡ ነጻው ፡ ዘመን ፡ አልቆ ስንት ፡ ሰው ፡ ዘምሯል ፡ ስንቱስ ፡ አጨብጭቧል በመከራው ፡ ቀን ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ብዙዎችን ፡ ታዝቧል ፡ ፡ :አዝ፦ ያዝ ፡ ለቀቅ እራሱን ፡ ላይገዛ ፡ ላይችል ፡ መታዘዙን በሞቅታ ፡ ጊዜ ፡ ቃል ፡ ኪዳነ ፡ ብዙ ሆኖለት ፡ ላይከፋል ፡ ስለት ፡ የተሳለ አሁን ፡ በዚህ ፡ መሃል ፡ ባለዳ ፡ ስንት ፡ አለ? ፡ ፡ :አዝ፦ ያዝ ፡ ለቀቅ መና ፡ ካዘነበ ፡ ከምንጩ ፡ ካጠጣን ከአመድ ፡ አንስቶን ፡ ከረግረግ ፡ ካወጣን ካበላን ፡ ካጠጣን ፡ ካከበረን ፡ ኋላ መስቀሉን ፡ አንሽሽ ፡ አብረን ፡ እንጉላላ ፡ ፡ :አዝ፦ ያዝ ፡ ለቀቅ