Loading
Singer
የፍቅርህ ፡ ልክ ፡ የፍቅርህ ፡ ገደብ በዝቶብኝ ፡ እኔስ ፡ ለማሰብ አይጠፋም ፡ ሥምህ ፡ ከአፌ አይወጣም ፡ ፍቅርህ ፡ ከልቤ (፪x) ቀስቃሽ ፡ አልፈልግም ፡ ሳመልክህ መች ፡ በረደ ፡ ውስጤ ፡ ያ ፡ ፍቅርህ ሲነድ ፡ ይሰማኛል ፡ በላዬ እወድሃለሁኝ ፡ ጌታዬ (፪x) ኢየሱሴ ፡ ለኔ ፡ ምትክ ፡ የለህ ልቤም ፡ ሌላ ፡ አይሻ ፡ አንተ ፡ እያለህ ከፍ ፡ የምታደርግ ፡ በአንተ ፡ ጊዜ ዙፋንህ ፡ ሥር ፡ ልስገድ ፡ ሁልጊዜ ተባረካ ፡ ጌታዬ ፡ ተባርክ ተባረካ ፡ አምላኬ ፡ ተባረክ (፪x) ምን ፡ ይከፈልሃል ፡ ጌታዬ ፡ (አሃሃ) ፡ ጌታዬ ሁሉ ፡ የአንተ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ (አሃሃ) ፡ አምላኬ ምሥጋናና ፡ አምልኮ ፡ አምልኮ ፡ (አሃሃ) ፡ ምሥጋና መቼ ፡ ይበዛብሃል ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ (አሃሃ) ፡ ገናና ተመስገንልኝ ፡ ጌታዬ ፡ ተመስገንልኝ ከሕያዋን ፡ ጋር ፡ ሥምህን ፡ አከብራለሁኝ ተባረክልኝ ፡ ጌታዬ ፡ ተባረክልኝ ከሚወዱህ ፡ ጋር ፡ ሥምህን ፡ አከብራለሁኝ እንዳለፈ ፡ ውሃ ፡ መከራዬን ረስቼዋለሁ ፡ ሳየው ፡ ጌታን እኔስ ፡ አልሰጋም ፡ ከእንግዲህስ ፡ ብዬ እዚህ ፡ ያደረስኝ ፡ አለ ፡ ጌታዬ አለ ፡ ጌታዬ ፡ (አለ) (፰x)