Loading
የማልተወው ቅኔ የማልተወው ቦታ ማልረሳው ልማዴ የህይወቴ ተርታ ካንተ ጋር መሆን ነው መክረም ባለህበት የህይወቴ ዋና የእስትንፋሴ ርዝመት ካንተ ጋር መሆን ነው መክረም ባለህበት የህይወቴ ዋና የእስትንፋሴ ርዝመት ካልደገፍከኝ ማልቆም ካልያዝከኝ የምወድቅ ካልመራኸኝ የምስት ካላንተ የማልደምቅ ሳትፈቅድልኝ የማልኖር የሆንክ እስትንፋሴ ሁሉዬ ነህ እየሱሴ ሳትፈቅድልኝ የማልኖር የሆንክ እስትንፋሴ ሁሉዬ ነህ እየሱሴ የሁሌ መናዬ ከላይ የወረድህ በደረቅ መሬት ላይ ነፍሴን ያረጠብህ ከሙታኖች ሰፈር ትንፋሽ ከሌለበት ሆንክልኝ ድልድዬ አብን ምደርስበት ሆንክልኝ ገመዴ አብን ምደርስበት ስምህን ጠራሁ ደስ አለኝ ቃልህን በላው ደስ አለኝ መንፈስህ አጽናናኝ ቀለለኝ አብሬህ ዋልኩኝ ደስ አለኝ አንተን አግኝቼ ሌላ መሄጃ አላስፈለገኝ አንተን ሰምቼ ሌላ የሚወራም አላስፈለገኝ ባንተ ተጽናናው ሌላ ሲጨመር አላስደሰተኝ ካንተጋ ቀየው ሌላ የሚያጽናና አላስፈለገኝ ብቻህን በቃኸኝ/8
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.