Loading
Singer
እያሳሳቀ ፡ ይወስዳል ፡ ውኃ ወደ ፡ ሙት ፡ አገር ፡ ወደ ፡ በረሃ እዳር ፡ ዳር ፡ ማለት ፡ በኃጥያት ፡ ሰፈር ወድቆ ፡ ለማንባት ፡ ለመሰባበር ሽሽ ፡ እንጂ ፡ ማነው ፡ ያለህ ፡ ተጠጋ በጠላትህ ፡ ቀስት ፡ እንዳትወጋ ኃጢአት ፡ አይምርም ፡ አንተን ፡ አግኝቶ የሚሻለው ፡ ግን ፡ ማምለጥ ፡ ነው ፡ ሸሽቶ ይቅርብህ ፡ እንዲያው ፡ በዋል ፡ ፈሰስ ይቅርብህ ፡ በሕይወት/በነፍስ ፡ ላይ ፡ አመፅ ይቅርብህ ፡ እንዲያው ፡ ወጣ ፡ ገባ ዕድሜህን ፡ አታድርገው ፡ የእንባ (፪x) ቅጥርን ፡ የሚያፈርስ ፡ እንደሚነደፍ ከፅድቅ ፡ ክሌ ፡ አትውጣ ፡ አትለፍ እንደ ፡ ተራበ ፡ ሆኖ ፡ እንደ ፡ አንበሳ ይጠብቅሃል ፡ ክፉ ፡ እያገሳ ፈቀቅ ፡ ብትል ፡ አንዲት ፡ እርምጃ መመለስህን ፡ መምጣትህን ፡ እንጃ የተከፈተው ፡ የአውሬው ፡ መንጋጋ ውጦ ፡ ያስቀርሃል ፡ አትዘናጋ መለስ ፡ እስኪ ፡ አንዴ ፡ በል ፡ መለስ አስብ ፡ በእርጋታ አይሻልም ፡ ዎይ ፡ መኖር ፡ በጌታ የሚያስጐመጀው ፡ ሁሉ ፡ አይበላ ሞትን ፡ ደብቆ ፡ ይዟል ፡ ከኋላ አትንካ ፡ ካለህ ፡ ቅዱስ ፡ አምላክህ ስለሚያውቅ ፡ ነው ፡ አስተውል ፡ ባክህ እሳትን ፡ እሳት ፡ አቅፎ ፡ በጉያው በአንዲት ፡ ሌሊት ፡ ነዶ ፡ ይጋያል ኃጢአት ፡ አድብቶ ፡ ቆሟል ፡ በደጅህ እባክህ ፡ አትተኛ ፡ ነቃ ፡ በል ፡ እንጂ ይቅርብህ ፡ እንዲያው ፡ በዋል ፡ ፈሰስ ይቅርብህ ፡ በሕይወት/በነፍስ ፡ ላይ ፡ አመፅ ይቅርብህ ፡ እንዲያው ፡ ወጣ ፡ ገባ ዕድሜህን ፡ አታድርገው ፡ የእንባ (፪x) ይቅርብህ (፫x)