Loading
Singer
ጌጤ ፡ ወርቄ ፡ ውበቴ ፡ ደም ፡ ግባቴ ኢየሱሴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሽልማቴ (2) ሽልማቴ ፡ ሽልማቴ ኢየሱሴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሽልማቴ (2) ከ ፡ ነገድ ፡ ቋንቋ ፡ በ ፡ ልጁ ፡ የዋጀኝ ወደከበረ ፡ መንግስቱ ፡ ያፈለሰኝ ከላይ ፡ ሲመጣ ፡ የተቀበልኩት ፡ ስጦታዬ ወራሽ ፡ አረገኝ ፡ የ ፡ እርስቱ ፡ ተካፋይ (5) ሽልማቴ ፡ ሽልማቴ ኢየሱሴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሽልማቴ (2) እኔን ፡ ለማድረግ ፡ ባለጠጋ ፡ ሆነህ ፡ ባዶ ውበት ፡ ሊሰጠኝ ፡ በኔ ፡ ምትክ ፡ ተሰቃይቶ በሰማያዊ ፡ በረከቱ ፡ ባረከኝ በ ፡ ጸጋው ፡ ሙላት ፡ በ ፡ መንፈሱ ፡ ከበበኝ (5) ሽልማቴ ፡ ሽልማቴ ኢየሱሴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሽልማቴ (2) የታረደው ፡ ኢየሱስ ፡ ፋሲካዬ የሞትን ፡ ጣር ፡ ገፈፈልኝ ፡ ከላዬ ዳግም ፡ ህይወት ፡ አገኘሁ ፡ ታደስኩኝ የ ፡ እግዚአብሄር ፡ ልጅ ፡ በመሆን ፡ ጸደኩኝ አ ፡ ሃ ፡ ሃ ፡ ጸደኩኝ (2) አ ፡ ሃ ፡ ሃ ፡ ከፍ ፡ አልኩኝ (2) አ ፡ ሃ ፡ ሃ ፡ ከበርኩኝ (2) አ ፡ ሃ ፡ ሃ (2) ማንም ፡ የተጠማ ፡ ይምጣና ከ ፡ ህይወት ፡ ውሃ ፡ ይጠጣና በ ፡ ሰላም ፡ ይኑር ፡ በ ፡ እርጋታ ብሎ ፡ ተናግሮአል ፡ ይሄ ፡ ጌታ እኔም ፡ ሰማሁት ፡ ወዳጄን የ ፡ ህይወት ፡ መንገድ ፡ መሪዬን ውጬዋለሁኝ ፡ መድሃኒቴን አትርፌአታለሁ ፡ ይህች ፡ ነፍሴን ሽልማቴ ፡ ሽልማቴ ኢየሱሴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሽልማቴ (2)