Loading
በእንባ ፡ እንዳልዘራሁ በለቅሶ ፡ እንዳልወጣሁ በሃዘን ፡ እንዳላለፍኩ ነዶዬን ፡ ይዤ ፡ ተመለስኩ መልካምነትህን ፡ አየው ጻድቅነትህን ፡ አየሁ በእንባ ፡ እንዳልነበርኩ ነዶዬን ፡ ይዤ ፡ ተመለስኩ ይኸው ፡ ምስጋናዬን ፡ እንካ ይኸው ፡ አምልኮዬን ፡ እንካ ይኸው ፡ ዝማሬዬን ፡ እንካ ይኸው ፡ እልልታዬን ፡ እንካ ባንተ ፡ አይደለም ፡ ወይ (፰x) ስደክም ፡ ያኔ ፡ ዝዬ ስበረታም ፡ ደግሞ ፡ ደግሜ ቁልቁለት ፡ ዳገቱ ፡ ሲያዝለኝ ሽቅብ ፡ መውጣቱ ፡ ሲከብደኝ የማያልፍ ፡ ሚመስልን ፡ ያን ፡ ዳገት አልፌው ፡ ስገኝ ፡ ድንገት አልረሳም ፡ ያን ፡ ቀውጢ ፡ ጊዜ ሲርቀኝ ፡ ሃዘን ፡ ትካዜ ይኸው ፡ ምስጋናዬን ፡ እንካ ይኸው ፡ አምልኮዬን ፡ እንካ ይኸው ፡ ዝማሬዬን ፡ እንካ ይኸው ፡ እልልታዬን ፡ እንካ ባንተ ፡ አይደለም ፡ ወይ (፰x) ማን ፡ አለው ፡ ብሎኛል ፡ ስደክም የተማመንኩበት ፡ ሲከስም የያዘኝ ፡ ጸጋህ ፡ በብርቱ በማልፍበት ፡ አልፎ ፡ የረዳኝ ፡ በሌቱ የብቸኝነቴ ፡ አምላክ የጓዳዬ ፡ የሚስጥሬ ፡ ጌታ ሰማህ ፡ ጩኸቴን ፡ ሰማህ ሰማህ ፡ እንባዬን ፡ ሰማህ ይኸው ፡ ምስጋናዬን ፡ እንካ ይኸው ፡ አምልኮዬን ፡ እንካ ይኸው ፡ ዝማሬዬን ፡ እንካ ይኸው ፡ እልልታዬን ፡ እንካ ባንተ ፡ አይደለም ፡ ወይ (፰x) ሽኩር ፡ ጉዌታ ፡ ሽኩር - ሽኩር (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.