Loading
Singer
አዝ:- ከጢሻ ፡ ከማጥ ፡ ውስጥ ፡ አውጥተህ በከበረ ፡ ስፍራ ፡ ላይ ፡ ታስቀምጣለህ ሰው ፡ ታደርጋለህ (ጌታ) ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (ኢየሱስ) ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (፪x) እንደ ፡ እኔ ፡ አይነቱን ፡ ክፉ ፡ ሰው ከኃጢአተኞች ፡ ሁሉ ፡ የባሰው እንዴት ፡ አሰብከኝ ፡ መረጥከኝ ምኔን ፡ አይተህ ፡ ነው ፡ የወደድከኝ የፍቅርህን ፡ ልክ ፡ ለመግለጽ ፡ ጌታዬ ፡ ቋንቋ ፡ የለኝም ከስግደት ፡ ከአምልኮ ፡ ሌላ ፡ የምሰጥህ ፡ እኔ ፡ ሌላ ፡ አላገኝም አዝ:- ከጢሻ ፡ ከማጥ ፡ ውስጥ ፡ አውጥተህ በከበረ ፡ ስፍራ ፡ ላይ ፡ ታስቀምጣለህ ሰው ፡ ታደርጋለህ (ጌታ) ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (ኢየሱስ) ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (፪x) እናት ፡ አባት ፡ ሆነኀኛል ፡ እውነተኛ ፡ ወላጅ ፡ ሆንከኝ እያበላህ ፡ እያጠጣህ ፡ በእቅፍህ ፡ ላይ ፡ አሳደከኝ ውለታህ ፡ ዝም ፡ አያሰኝም ፡ የደስታ ፡ እምባ ፡ ያመጣል ያ ፡ ብዙ ፡ ቸርነትህ ፡ ቢወራ ፡ መቼ ፡ ያልቃል አዝ:- ከጢሻ ፡ ከማጥ ፡ ውስጥ ፡ አውጥተህ በከበረ ፡ ስፍራ ፡ ላይ ፡ ታስቀምጣለህ ሰው ፡ ታደርጋለህ (ጌታ) ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (ኢየሱስ) ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (፪x) እኔን ፡ ከድጥ ፡ ላይ ፡ ለማንሳት ፡ ከማንም ፡ ጋር ፡ አልተማከርክ ልጄ ፡ ነው ፡ ወልጄሃለሁ ፡ ለማለትም ፡ በእኔ ፡ አላፈርክ በድኔን ፡ አፈር ፡ ልታለብስ ፡ ኑሮዬ ፡ እንዲሆን ፡ ምድር ፡ ሥር ትንሳኤ ፡ ልትሰጠኝ ፡ እንጂ ፡ አልመጣህ ፡ እኔን ፡ ልትቀብር አዝ:- ከጢሻ ፡ ከማጥ ፡ ውስጥ ፡ አውጥተህ በከበረ ፡ ስፍራ ፡ ላይ ፡ ታስቀምጣለህ ሰው ፡ ታደርጋለህ (ጌታ) ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (ኢየሱስ) ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (፪x) ያለ ፡ መታሰቢያ ፡ እንዳልቀር ፡ ሲኦል ፡ እንዳልወረወር የሰይጣን ፡ መጫወቻ ፡ እንዳልሆን ፡ እንዳልፈጅብህ ፡ በእቶን በሕይወት ፡ መዝገብ ፡ ላይ ፡ ስሜን ፡ በከበረው ፡ ደምህ ፡ ጻፍከው አቤት ፡ የተረሳውን ፡ ሰው ፡ ደግመህ ፡ ወልደህ ፡ ሰው ፡ አደረከው አዝ:- ከጢሻ ፡ ከማጥ ፡ ውስጥ ፡ አውጥተህ በከበረ ፡ ስፍራ ፡ ላይ ፡ ታስቀምጣለህ (ጌታ) ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (ኢየሱስ) ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (፪x) ሰው ፡ ታደርጋለህ (ጌታ) ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (ኢየሱስ) ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (፪x)