Loading
Singer
ማንም ፡ ወንድሙን ፡ አይናቀው (፪x) ያገኘም ፡ ያጣ ፡ ሰው ፡ ክቡር ፡ ነው (፪x) ማንም ፡ ታናሹን ፡ አይናቀው (፪x) ያገኘም ፡ ያጣ ፡ ሰው ፡ ክቡር ፡ ነው (፪x) ለምን ፡ ተስፋ ፡ ይቁረጥ ፡ ለምንስ ፡ ይቆዝም ዳቦ ፡ አይሁንበት ፡ አይራበው ፡ ፍቅር ወንድሜ ፡ መገለሉ ፡ ይቅር (፫x) ከእናቴም ፡ ባይወለድ የአዳም ፡ ዘር ፡ የእግዜር ፡ ፍጡር አብሬው ፡ ልቁረስ ፡ ልስጠው እኔ ፡ በልቼ ፡ አይራበው አያሳዝንም ፡ ወይ ፡ የራበው ፡ ሳያንሰው አያሳዝንም ፡ ወይ ፡ ፍቅር ፡ ሲቸግረው አያሳዝንም ፡ ወይ ፡ ጥግ ፡ ይዞ ፡ ሲያለቅስ አያሳዝንም ፡ ወይ ፡ አንጀቱ ፡ ሲላወስ መጽናናቱ ፡ (ልሁንለት ) እኔ ፡ እያለሁ ፡ (ወንድሜ ፡ አይሙት) ትላንትና ፡ (እንዴት ፡ ይረሳል) አፈር ፡ ባፈር ፡ (ላይ ፡ እንዴት ፡ ይኮራል) አያሳዝንም ፡ ወይ ፡ የራበው ፡ ሳያንሰው አያሳዝንም ፡ ወይ ፡ ፍቅር ፡ ሲቸግረው አያሳዝንም ፡ ወይ ፡ ጥግ ፡ ይዞ ፡ ሲያለቅስ አያሳዝንም ፡ ወይ ፡ አንጀቱ ፡ ሲላወስ መፅናናቱ ፡ (ልሁንለት) እኔ ፡ እያለሁ ፡ (ወንድሜ ፡ አይሙት) ትላንትና ፡ (እንዴት ፡ ይረሳል) አፈር ፡ ባፈር ፡ (ላይ ፡ እንዴት ፡ ይኮራል) ባልንጀራህን ፡ እንደራስህን ፡ ውደድ ለራስህ ፡ የክብር ፡ ወንበር ፡ አትውሰድ ጌታው ፡ ሲፈርድ ፡ ኋላ ፡ እንዳትወሰድ ባልንጀራህን ፡ እንደራስህን ፡ ውደድ ለራስህ ፡ ክብር ፡ ወንበር ፡ አትውሰድ (፪x)