Loading
Singer
ሰው ፡ ሁሉ ፡ ነፍሱን ፡ ቢያተርፍ ፡ ለሥጋው መዝገቡ ፡ ቢሆን ፡ እዚህ ፡ ምድራዊ ምን ፡ ይረባዋል ፡ ምንስ ፡ ሊጠቅመው ሕይወትን ፡ ትቶ ፡ መሆኑ ፡ ጠፊ ፡ ሰው አዝ፦ ሰው ፡ ሆይ ፡ ክብርን ፡ ሰው ፡ ሆይ ፡ አትይ ዕውቀት ፡ ጥበብን ፡ የዓለምን ፡ ዝና እንቅፋት ፡ ሆኖ ፡ ጋሬጣ ፡ ሆኖ ከአምላክህ ፡ እንዳይለይህ (፪x) የእግዚአብሔር ፡ አምሳል ፡ ክብር ፡ ያለበት ሰው ፡ ውድ ፡ ነበረ ፡ እርሱ ፡ ቢያውቅበት በገነት ፡ ምድር ፡ ሊኖር ፡ በደስታ ነበር ፡ አላማው ፡ ሲፈጥረውማ ፡ ጌታ አዝ፦ ሰው ፡ ሆይ ፡ ክብርን ፡ ሰው ፡ ሆይ ፡ አትይ ዕውቀት ፡ ጥበብን ፡ የዓለም ፡ ዝና እንቅፋት ፡ ሆኖ ፡ ጋሬጣ ፡ ሆኖ ከአምላክህ ፡ እንዳይለይህ (፪x) ብናኝ ፡ አቧራ ፡ ውዳቂ ፡ ጠፊ ነው ፡ የሰው ፡ ትምክቱ ፡ ደግሞም ፡ አላፊ ሰው ፡ ሆይ ፡ ከአምላክህ ፡ ብትስማማ በርሱ ፡ እጅ ፡ ነበር ፡ ብሩና ፡ ወርቁማ አዝ፦ ሰው ፡ ሆይ ፡ ክብርን ፡ ሰው ፡ ሆይ ፡ አትይ ዕውቀት ፡ ጥበብን ፡ የዓለም ፡ ዝና እንቅፋት ፡ ሆኖ ፡ ጋሬጣ ፡ ሆኖ ከአምላክህ ፡ እንዳይለይህ (፪x)