Loading
Singer
አዝ፦ ሰው ፡ እንደፀና አይቆይ ፡ ሆኖ ፡ ገናና ጉልበቱ ፡ ይክደዋል ንብረት ፡ ሃብቱ ፡ ይሸሸዋል ፡ ይረሳል (፪x) አምላኬ ፡ ግን ፡ እንዲህ ፡ አይደለም ጌታ ፡ ግን ፡ እንዲህ ፡ አይደለም (፪x) ለውበትህ ፡ ወደር ፡ የለው (፪x) በሰማይ ፡ በምድር ፡ መሳይ ፡ የለው (፪x) ኃይሉ ፡ ከሁሉ ፡ የበረታ (፪x) የጌቶች ፡ ሁሉ ፡ ነው ፡ ጌታ (፪x) ለማንም ፡ አለ ፡ ሳይረታ (፪x) አዝ፦ ሰው ፡ እንደፀና አይቆይ ፡ ሆኖ ፡ ገናና ጉልበቱ ፡ ይከብደዋል ንብረት ፡ ሃብቱ ፡ ይሸሸዋል ፡ ይረሳል (፪x) አምላኬ ፡ ግን ፡ እንዲህ ፡ አይደለም ጌታ ፡ ግን ፡ እንዲህ ፡ አይደለም (፪x) ብርቱ ፡ ኃያላኖች ፡ ተነሱ (፪x) ሞት ፡ አይቀርምና ፡ ተረሱ (፪x) እርጅና ፡ ድካም ፡ የማያውቀው (፪x) ጥበብ ፡ ዕውቀቱ ፡ የጠለቀው (፪x) ባለ ፡ ብዙ ፡ ክብር ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x) አዝ፦ ሰው ፡ እንደፀና አይቆይ ፡ ሆኖ ፡ ገናና ጉልበቱ ፡ ይከብደዋል ንብረት ፡ ሃብቱ ፡ ይሸሸዋል ፡ ይረሳል (፪x) አምላኬ ፡ ግን ፡ እንዲህ ፡ አይደለም ጌታ ፡ ግን ፡ እንዲህ ፡ አይደለም (፪x) የተነሱበትን ፡ ያዋርዳል (፪x) ትዕቢተኞችን ፡ ይቀጣል (፪x) የተፈሩትን ፡ የማይፈራ (፪x) ዓይናቸው ፡ እያየ ፡ አለ ፡ እየሰራ (፪x) እየናደ ፡ ግዙፉን ፡ ተራራ (፪x) አዝ፦ ሰው ፡ እንደፀና አይቆይ ፡ ሆኖ ፡ ገናና ጉልበቱ ፡ ይከብደዋል ንብረት ፡ ሃብቱ ፡ ይሸሸዋል ፡ ይረሳል (፪x) አምላኬ ፡ ግን ፡ እንዲህ ፡ አይደለም ጌታ ፡ ግን ፡ እንዲህ ፡ አይደለም (፪x) ብቻውን ፡ ተዓምራት ፡ ያደርጋል (፪x) ያለ ፡ ሠራዊት ፡ ይዋጋል (፪x) በድል ፡ ላይ ፡ ድልን ፡ እያገኘ (፪x) ጠላቶቹን ፡ አዋርዶ ፡ እየሸኘ (፪x) አንድ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ የተገኘ (፪x) አዝ፦ ሰው ፡ እንደፀና አይቆይ ፡ ሆኖ ፡ ገናና ጉልበቱ ፡ ይከብደዋል ንብረት ፡ ሃብቱ ፡ ይሸሸዋል ፡ ይረሳል (፪x) አምላኬ ፡ ግን ፡ እንዲህ ፡ አይደለም ጌታ ፡ ግን ፡ እንዲህ ፡ አይደለም (፪x)