Loading
ሥራዬን የሠራህልኝ መንገዴን ያቀናህልኝ (፪x) አማኑኤል ከፍ በልልኝ (፫x) ኢየሱሴ ከፍ በልልኝ የእኔ ጌታ ከፍ በልልኝ ተራራውን ንዶ ሜዳ ከአደረገው መራመድ ብቻ ነው ከእኔ ሚጠበቀው (፪x) ጐዳናዬ ቀንቶ ተራመድ ብሎኛል ከእኔ ጋር ስላለ ማን ይቃወመኛል (፪x) ማን ይቃወመኛል (፪x) የቱ ይይዘኛል (፪x) አልፈራም ልቤ አይሰጋ ጌታዬ አለ ከእኔ ጋ አልፈራም ልቤ አይሰጋ የጠራኝ አለ ከእኔ ጋ አይቆምም ምንም ከፊቴ እግዚአብሔር ነው ዛሬም ጉልበቴ (፭x) ሰባሪው እግዚአብሔር ከፊት ወጥቷልና ሃሳቤ ተሳክቶ መንገዴም ተቃና (፪x) የነሃሱን ደጆች በስልጣን ሰበረው እኔም ሰባብሬ ከእርሱ ጋር አልፌያለው (፪x) ከእርሱ ጋር አልፌያለው (፬x) አልዝልም እኔ አልደክምም ስራዬ አያሰለችም (፪x) ቅባቱ በእኔ ስላለ ይሄዳል እየጨመረ (፭x) ታማኝ ነው የጠራኝ ጌታ ለምንም ትጥቄ አይፈታ (፪x) ብርቱ ነው በቃሉ የፀና ይመራኛል በድል ጐዳና (፭x) ከፍ በል ብል ሁልጊዜ ይሄ መች ይበቃሃል (፫x) ተባረክ ብል ሁልጊዜ ይሄ መች ይበቃሃል (፫x) ተመለክ ብል ሁልጊዜ ይሄ መች ይበቃሃል (፫x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.