Loading
Singer
አዝ፦ በዘመን ፡ በዓመታት ፡ መሃል ሥራህን ፡ ትፈፅማለህ የሚከለክልህ ፡ ማነው ኢየሱስ ፡ ኃይልህ ፡ ብርቱ ፡ ነው (፪x) ባለፈው ፡ ዘመን ፡ የሰራ ፡ ዛሬም ፡ ክንዱ ፡ ያልደከመ መንግሥቱን ፡ በደንብ ፡ አስፋፋ ፡ እኛም ፡ ደግሞ ፡ የቀጠለ ኃይል ፡ ብርታት ፡ ጉልበት ፡ ሆኖልን ፡ የምንሰራው ፡ አብረን ፡ ነው አሁን ፡ ካሳየን ፡ ይበልጣል ፡ ነገን ፡ በእኛ ፡ የሚገልጠው ሰራተኛ ፡ አድርጐናል ፡ ለቤቱ መስራት ፡ ያላቆመ ፡ ከጥንቱ በሚሰራበት ፡ ቀን ፡ በቤቱ መጠቀሚያው ፡ ነን ፡ እኛ ፡ ገንዘቡ (፪x) አዝ፦ በዘመን ፡ በዓመታት ፡ መሃል ሥራህን ፡ ትፈፅማለህ የሚከለክልህ ፡ ማነው ኢየሱስ ፡ ኃይልህ ፡ ብርቱ ፡ ነው (፪x) በአሁኑ ፡ ዓመት ፡ እንዳየነው ፡ በሚመጣው ፡ ዓመት ፡ አይሆንም ብሶበት ፡ እንጂ ፡ ቀንሶ ፡ ሥራው ፡ አይከናወንም እጥፍ ፡ ድርብ ፡ እየሆነ ፡ ፍሬው ፡ ገና ፡ ይበዛልናል በክልል ፡ አይወሰንም ፡ የምድርን ፡ ፊት ፡ ይሸፍናል የምሩን ፡ ይነሳል ፡ ንጉሡ እናንተ ፡ አገልጋዮች ፡ ተነሱ ገና ፡ ብዙ ፡ ጉድ ፡ ነው ፡ የሚታየው እግዚአብሔር ፡ ሀሳቡ ፡ እኛ ፡ ላይ ፡ ነው (፪x) አዝ፦ በዘመን ፡ በዓመታት ፡ መሃል ሥራህን ፡ ትፈፅማለህ የሚከለክልህ ፡ ማነው ኢየሱስ ፡ ኃይልህ ፡ ብርቱ ፡ ነው (፪x) ዛሬ ፡ ከተገለጠልን ፡ የነገው ፡ ደግሞ ፡ ይብሳል የሚመጣልን ፡ ዝማሬ ፡ የዛሬን ፡ ሁሉ ፡ ያስረሳል ማሽቆልቆል ፡ ወደታች ፡ መውረድ ፡ መቀነስ ፡ መዳከም ፡ መዛል ከዚህ ፡ በኋላ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ በኢየሱስ ፡ ሥም ፡ አይሰራም ተሻገር ፡ የሚል ፡ ወደ ፡ ማዶ ሰምተናል ፡ ድምፅ ፡ ከሰማይ ፡ ወርዶ ተሻግረን ፡ ደግሞ ፡ እንሄዳለን የነገውን ፡ ዘመን ፡ እናያለን (፪x) አዝ፦ በዘመን ፡ በዓመታት ፡ መሃል ሥራህን ፡ ትፈፅማለህ የሚከለክልህ ፡ ማነው ኢየሱስ ፡ ኃይልህ ፡ ብርቱ ፡ ነው (፪x)