Loading
Singer
በመከራዬ ፡ ቀን ፡ ላልተለየኝ አበሳዬን ፡ ከኔ ፡ ላራቀልኝ ለዚህ ፡ ለጌታዬ ፡ እሰግዳለሁ ሁልጊዜ ፡ ምሥጋናን ፡ አበዛለሁ ዘምርለታለሁ (፭x) ፡ ለአባቴ ፡ ዘምርለታለሁ አዝ፦ ስንቱን ፡ ላውራው ፡ ልተርከው አንተ ፡ ያደረከው ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ጌታ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው (፬x) ፊትለፊት ፡ ቆሞ ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ ተራራ የመድሃኒቴ ፡ አምላክ ፡ ስልህ ፡ ሰማኸኝ ፡ ስጣራ በተራራዬ ፡ ላይ ፡ በድል ፡ አራመድከኝ ከሳሶቼ ፡ እያዩ ፡ አሜን ፡ ተስፋዬን ፡ ወረስኩኝ ተስፋዬን ፡ ሰበርኩት አዝ፦ ስንቱን ፡ ላውራው ፡ ልተርከው አንተ ፡ ያደረከው ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ጌታ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው (፬x) ተስፋዬን ፡ ቆርጬ ፡ ለሰው ፡ ያልነገርኩት አበቃለት ፡ ብዬ ፡ ሞቶ ፡ የቀበርኩት ምንተስኖህ ፡ ጌታ ፡ ሁሉ ፡ ተችሎሃል አንገት ፡ ያስደፋኝን ፡ ቀንበሬን ፡ ሰብረሃል ፡ ጌታ ቀንበሬን ፡ ሰብረሃል አዝ፦ ስንቱን ፡ ላውራው ፡ ልተርከው አንተ ፡ ያደረከው ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ጌታ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው (፬x) አዋጅ ፡ ሲል ፡ ጠላቴ ፡ እኔን ፡ ሊያጠፋ ከበሮ ፡ ሲያስደልቅ ፡ ነጋሪት ፡ ሲያስመታ በአንድ ፡ ሌሊት ፡ ጀምበር ፡ ታሪክ ፡ ተቀየረ ጠላት ፡ በቆፈረው ፡ አሜን ፡ ጉድጓድ ፡ ተቀበረ ፡ እሰይ ጉድጓድ ፡ ተቀበረ በመከራዬ ፡ ቀን ፡ ላልተለየኝ (ላልተለየኝ) አበሳዬን ፡ ከኔ ፡ ላራቀልኝ (ላራቀልኝ) ለዚህ ፡ ለጌታዬ ፡ እሰግዳለሁ ሁልጊዜ ፡ ምሥጋናን ፡ አበዛለሁ ፡ ዘምርለታለሁ አዎ ዘምርለታለሁ ፡ (ዘምርለታለሁ) (፪x) ዘምርለታለሁ ፡ ለአባቴ ፡ ዘምርለታለሁ (አቤት ፡ አቤት) አዝ፦ ስንቱን ፡ ላውራ (ላውራ) ፡ ልተርከው (ልተርከው) አንተ ፡ ያደረከው (ያደረከው) ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ጌታ (በላይ ፡ በላይ ፡ ነው) ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው (፬x) (በላይ ፡ በላይ)