Loading
Singer
አንድ ፡ ነገር ፡ በጣም ፡ ገብቶኛል ፡ በሕይወት ፡ ዘመኔ የዛለው ፡ በአንተ ፡ ሲበረታ ፡ አይቻለሁ ፡ በዓይኔ ተቆትተህ ፡ በዛው ፡ አትቀርም ፡ እስከ ፡ መጨረሻው ቢወድቅም ፡ ይነሳል ፡ ፃዲቁ ፡ ስላለው ፡ መድረሻ አዝ፦ ስንት ፡ ጊዜ ፡ አነሳኸኝ ስንት ፡ ጊዜ ፡ አቅም ፡ ሆንከኝ ስንት ፡ ጊዜ ፡ ጨለማዬን ከደንከው ፡ በብርሃን ስንት ፡ ጊዜ ፡ ስደክምብህ ስንት ፡ ጊዜ ፡ ያዘኝ ፡ ፀጋህ ስንት ፡ ጊዜ ፡ ከጠላት ፡ ዛቻ ከለለኝ ፡ ምህረትህ ፡ ብቻ (፭x) ያንን ፡ ጭጋግ ፡ ደመናውን ያን ፡ በረሃ ፡ ሃሩሩን በአንተ ፡ ጉልበት ፡ አልፌዋለሁ በማሳለፍ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ማነው ያን ፡ ኃጢያቴን ፡ ቁሻሻውን ያንን ፡ ልብሴን ፡ እድፋሙን ቀይረህ ፡ ከሞት ፡ ወጥቻለሁ በማስወጣት ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ማነው አዝ፦ ስንት ፡ ጊዜ ፡ አነሳኸኝ ስንት ፡ ጊዜ ፡ አቅም ፡ ሆንከኝ ስንት ፡ ጊዜ ፡ ጨለማዬን ከደንከው ፡ በብርሃን ስንት ፡ ጊዜ ፡ ስደክምብህ ስንት ፡ ጊዜ ፡ ያዘኝ ፡ ፀጋህ ስንት ፡ ጊዜ ፡ ከጠላት ፡ ዛቻ ከለለኝ ፡ ምህረትህ ፡ ብቻ (፭x) ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ማነሳሳህ ፡ ደጋግሜ በተከበበው ፡ ከተማማ ፡ ለእኔ ፡ ይገርመኛል ፡ መቆሜ ስለዚህ ፡ በምሥጋና ፡ ልውጣ ፡ ያረክልኝን ፡ ቆጥሬ ሳላስበው ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ አይቻለሁና ፡ ከብሬ አዝ፦ ስንት ፡ ጊዜ ፡ አነሳኸኝ ስንት ፡ ጊዜ ፡ አቅም ፡ ሆንከኝ ስንት ፡ ጊዜ ፡ ጨለማዬን ከደንከው ፡ በብርሃን ስንት ፡ ጊዜ ፡ ስደክምብህ ስንት ፡ ጊዜ ፡ ያዘኝ ፡ ፀጋህ ስንት ፡ ጊዜ ፡ ከጠላት ፡ ዛቻ ከለለኝ ፡ ምህረትህ ፡ ብቻ (፭x) አባትዬ ፡ ኢየሱስዬ አልከሰርኩም ፡ እኔ ፡ አንተን ፡ ብዬ እኔ ፡ አንተን ፡ ብዬ (፪x) እኔ ፡ አንተን ፡ ብዬ (፬x)