Loading
Singer
በሃዘን ፡ ፈንታ ፡ ደስታ በለቅሶም ፡ ምትክ ፡ ዕልልታ ሁሉንም ፡ መልካም ፡ አደረገው ክፉውን ፡ ለበጐ ፡ ቀየረው (፪x) አዝ፦ ምን ፡ ልበል ፡ ሌላማ ፡ ሌላማ ምሥጋናዬን/አምልኮዬን ፡ ለጌታ ፡ ላሰማ (፪x) በምሥጋና ፡ ስሙን ፡ አከብራለሁ (፪x) እጅግ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ለእኔ ፡ ያደረገው ፣ ለእኔ ፡ ያደረገው እጅግ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ለእኔ ፡ ያደረገው ፣ ለእኔ ፡ ያደረገው የተዘጋውን ፡ ደጅ ፡ ከፈተው የነሃሱንም ፡ መዝጊያ ፡ ሰበረው መወርወሪያዎቹን ፡ ቆራርጦ አሳለፈኝ ፡ ከፊቴ ፡ ወጥቶ አዝ፦ ምን ፡ ልበል ፡ ሌላማ ፡ ሌላማ ምሥጋናዬን/አምልኮዬን ፡ ለጌታ ፡ ላሰማ (፪x) በምሥጋና ፡ ስሙን ፡ አከብራለሁ (፪x) እጅግ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ለእኔ ፡ ያደረገው ፣ ለእኔ ፡ ያደረገው እጅግ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ለእኔ ፡ ያደረገው ፣ ለእኔ ፡ ያደረገው በከበረው ፡ ደሙ ፡ ቀድሶ መንፈሱን ፡ በላዬ ፡ አፍሶ ሕይወቴን ፡ በፍቅሩ ፡ ቀየረው ታሪኬን ፡ እንዲህ ፡ አሳመረው (፪x) አዝ፦ ምን ፡ ልበል ፡ ሌላማ ፡ ሌላማ ምሥጋናዬን/አምልኮዬን ፡ ለጌታ ፡ ላሰማ (፪x) በምሥጋና ፡ ስሙን ፡ አከብራለሁ በምሥጋና ፡ ስሙን ፡ አከብራለሁ እጅግ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ለእኔ ፡ ያደረገው ፣ ለእኔ ፡ ያደረገው (፬x)