Loading
Singer
በሰነፍ ፡ ምክር ፡ ልቡ ፡ ተውጦ የጽድቅን ፡ መንገድ ፡ የሄደ ፡ አቋርጦ የሥጋን ፡ ለባሽ ፡ ደጅ ፡ እየጠና ዛሬም ፡ ይኖራል ፡ ሆኖ ፡ ጥገኛ ያ ፡ ሰው ፡ ያ ፡ ሰው ፊቱን ፡ ብፈልግ ፡ ደጁን ፡ ብጠና ኧረ ፡ አትዘን ፡ ብሎ ፡ ያረገኝ ፡ ቀና ዛሬም ፡ የሙጥኝ ፡ እርሱን ፡ እላለሁ የእኔስ ፡ ደጋፊ ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ካለው ፡ ተወለድ ፡ ወይ ፡ ካለው ፡ ተጠጋ የሚለው ፡ ተረት ፡ መች ፡ ይገባኛል ኢየሱስ ፡ ካለኝ ፡ ሁሉም ፡ እንዳለኝ ፡ መንፈስ ፡ ነግሮኛል በሰው ፡ የወጣ ፡ በሰው ፡ ይወርዳል የተሰጠውም ፡ በመንገድ ፡ ያልቃል የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ግን ፡ በምድረ ፡ በዳ ፡ ምንጭን ፡ ያፈልቃል (ስሙኝማ) ፡ የእኔ ፡ ደጋፊ (ስሙኝማ) ፡ ካለልኝ ፡ ከጐኔ (ስሙኝማ) ፡ ማንም ፡ ሰው ፡ ባይኖረኝ (ስሙኝማ) ፡ ምን ፡ ሊጨንቀኝ ፡ እኔ ሁሉን ፡ የሚያስንቅ ፡ በልጦ ፡ ሚተካ የልቤ ፡ ወዳጅ ፡ አለለኝ ፡ ጌታ አለልኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አለልኝ አለልኝ ፡ ኢየሱሴ ፡ አለልኝ በልምምጥ ፡ ቃል ፡ በአባባይ ፡ ቋንቋ ፡ ተቀለጣጥፎ ፡ ሰው ፡ የተጠጋ ፍጻሜ ፡ ሳይደርስ ፡ አንገቱን ፡ ደፍቶ ፡ ቆሟል ፡ እዛጋ የአምላኩን ፡ ፊት ፡ እየፈለገ ጌታን ፡ በመፍራት ፡ ተግቶ ፡ የኖረ ላይቆም ፡ ይሄዳል ፡ የጌታን ፡ ማዳን ፡ እየሰበከ ዘንድሮ ፡ ሆኗል ፡ ምላስ ፡ ላላቸው የሰው ፡ ደጋፊ ፡ ለበዛላቸው ብለው ፡ ለሚሉ ፡ ጌታ ፡ ልኮኛል ፡ እንዲህ ፡ እንድላቸው እነ ፡ ኤልያብ ፡ ሰልፍ ፡ እንደያዙ እኔን ፡ ብቀባኝ ፡ ብለው ፡ ሲጓጉ ጌታ ፡ የደገፈው ፡ ዳዊት ፡ ተቀባ ፡ እነሱ ፡ እያዩ (ስሙኝማ) ፡ የእኔ ፡ ደጋፊ (ስሙኝማ) ፡ ካለልኝ ፡ ከጐኔ (ስሙኝማ) ፡ ማንም ፡ ሰው ፡ ባይኖረኝ (ስሙኝማ) ፡ ምን ፡ ሊጨንቀኝ ፡ እኔ ሁሉን ፡ የሚያስንቅ ፡ በልጦ ፡ ሚተካ የልቤ ፡ ወዳጅ ፡ አለለኝ ፡ ጌታ አለልኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አለልኝ አለልኝ ፡ ኢየሱሴ ፡ አለልኝ በሥጋ ፡ ለባሽ ፡ ዓይኑን ፡ የጣለ አለኝ ፡ እከሌ ፡ ለሁሉ ፡ ያለ የተመካበት ፡ ድንገት ፡ ሲሰበር ፡ ዓይኔ ፡ ይሄን ፡ አየ ከዘመድ ፡ አዝማድ ፡ ዓይኑን ፡ ያነሳ በአምላኩ ፡ ታምኑ ፡ ከዑር ፡ የወጣ አንዱን ፡ ደጋፊ ፡ አብርሃም ፡ ይዞ ፡ ከቶ ፡ ምን ፡ አጣ (ስሙኝማ) ፡ የእኔ ፡ ደጋፊ (ስሙኝማ) ፡ ካለልኝ ፡ ከጐኔ (ስሙኝማ) ፡ ማንም ፡ ሰው ፡ ባይኖረኝ (ስሙኝማ) ፡ ምን ፡ ሊጨንቀኝ ፡ እኔ ሁሉን ፡ የሚያስንቅ ፡ በልጦ ፡ ሚተካ የልቤ ፡ ወዳጅ ፡ አለለኝ ፡ ጌታ አለልኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አለልኝ አለልኝ ፡ ኢየሱሴ ፡ አለልኝ