Loading
Singer
ስለ ፡ አንተ ፡ በጆሮዬ ፡ ከሰማሁት ፡ ይልቅ (፪x) በዓይኔ ፡ ያየሁት ፡ ለእኔ ፡ ሆነብኝ ፡ ድንቅ (፪x) የእኔ ፡ ጌታ ፡ ተባረክ ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፬x) እግዚአብሔር ፡ ለምን ፡ እንዲህ ፡ አረክ ፡ አይባልም (፪x) የሚሰራውን ፡ ያውቃል ፡ ፍፁም ፡ አይዘነጋም (፪x) የእኔ ፡ ጌታ ፡ ተባረክ ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፬x) ምሥጋናዬ (፬x) ይድረስ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ጌታዬ (፪x) እግዚአብሔር ፡ ህዝቡን ፡ መታደግን ፡ ያውቃል (፪x) ካስፈለገ ፡ ደግሞ ፡ ፀሐይን ፡ ያቆማል (፪x) የእኔ ፡ ጌታ ፡ ተባረክ ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፬x) እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ጌታ ፡ ነው ዓለም ፡ ሁሉ ፡ በሙሉ ፡ የእርሱ ፡ ነው (፪x) የእኔ ፡ ጌታ ፡ ተባረክ ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፬x) እግዚአብሔር ፡ አምላክን ፡ አትጠራጠሩት ያደርጋል ፡ ብላችሁ ፡ በእውነት ፡ እመኑት ስሙኝ ፡ እንጂ (፪x) እግዚአብሔር ፡ አምላክን ፡ አትጠራጠሩት ያደርጋል ፡ ብላችሁ ፡ በእውነት ፡ እመኑት ስሙኝ ፡ እንጂ (፪x) እስቲ ፡ ላስታውሳችሁ ፡ ትውስ ፡ አለኝ ፡ እኔም አምላኬ ፡ የሰራው ፡ ከዚህ ፡ ቀደም ስሙኝ ፡ እንጂ (፪x) የኤርትራን ፡ ባሕር ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ ከፈለው ውኃውን ፡ እንደ ፡ ግድግዳ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አቆመው ስሙኝ ፡ እንጂ (፪x) የመንፈስ ፡ የመንፈስ ፡ የመንፈሱን ፡ እንጂ የሥጋውን ፡ መስማት ፡ ያስጥላል ፡ ከደጅ ስሙኝ ፡ እንጂ (፪x) በምድረ ፡ በዳ ፡ ላይ ፡ ይህን ፡ ያደርጋል ከቶ ፡ ለምን ፡ አልከው ፡ አይቻለውም ፡ ወይ ስሙኝ ፡ እንጂ (፪x) ምሥጋናዬ (፬x) ይድረስ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ጌታዬ (፪x) አቤት ፡ ውበቱ ፡ የተዓምራቱ ለጠበቀው ፡ ሰው ፡ እስከ ፡ ሰዓቱ ሊመጣ ፡ ሲልም ፡ አረፋፈዱ ሊነጋ ፡ ሲልም ፡ መጨላለሙ አርፍዶ ፡ ይነሳል ፡ ሁሉን ፡ ይቀድማል የተዓምራቱን ፡ ውበት ፡ ያሳያል (፪x) አቤት ፡ ውበቱ ፡ የተዓምራቱ ለጠበቀው ፡ ሰው ፡ እስከ ፡ ሰዓቱ ሊመጣ ፡ ሲልም ፡ አረፋፈዱ ሊነጋ ፡ ሲልም ፡ መጨላለሙ አርፍዶ ፡ ይነሳል ፡ ሁሉን ፡ ይቀድማል የተዓምራቱን ፡ ውበት ፡ ያሳያል (፪x)