Loading
Singer
እንኳን ፡ ማንነቱ ፡ ሥሙ ፡ ሞገሳም ፡ ነው ወዶ ፡ አይደለም ፡ ፍጥረት ፡ ሰዎች ፡ የሚርበደበደው ከወዲህ ፡ ተጠርቶ ፡ ከማዶ ፡ ይሰራል ድንገት ፡ ደርሶ ፡ የጠላትን ፡ ምሽግ ፡ ያሸብራል አዝ፦ ኢየሱስ ፡ የሚለው ፡ ሥም ፡ ብርቱ ፡ ጉልበት ፡ አለበት አይቻለሁ ፡ ጠላቶቼ ፡ ሲመታ ፡ ሲያንቀጠቅጥ (፪x) እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ልክ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያረገው ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ሥምም ፡ የተሰጠው በሰማይም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው በምድርም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ከምድር ፡ በታች ፡ ኢየሱስ ፡ ነው በሁሉ ፡ ላይ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x) የበሽታ ፡ ብርታት ፡ የደዌ ፡ ጉልበት አይፈልግም ፡ የጌታ ፡ ሥም ፡ እንዲጠራበት በሥጋ ፡ ለባሽ ፡ ላይ ፡ የሚበረታው ያውቃል ፡ ከተጠራ ፡ ሥሙ ፡ እንደሚነቅለው አዝ፦ ኢየሱስ ፡ የሚለው ፡ ሥም ፡ ታላቅ ፡ ጉልበት ፡ አለበት አይቻለሁ ፡ ለህመሜ ፡ ሲሆን ፡ መድኃኒት (፪x) እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ልክ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያረገው ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ሥምም ፡ የተሰጠው በሰማይም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው በምድርም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ከምድር ፡ በታች ፡ ኢየሱስ ፡ ነው በሁሉ ፡ ላይ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x) የመከራን ፡ ጭጋግ ፡ የሚችል ፡ መግፈፍ በእውነተኛው ፡ በረከት ፡ የሚያትረፈርፍ የባዶ ፡ ሸለቆ ፡ የመሙላት ፡ ሚስጥር ሲጠራ ፡ ነው ፡ የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ በታላቅ ፡ ክብር አዝ፦ ኢየሱስ ፡ የሚለው ፡ ሥም ፡ ደግነትም ፡ አለበት አይቻለሁ ፡ በጓዳዬ ፡ ሲሆንልኝ ፡ በረከት (፪x) እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ልክ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያረገው ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ሥምም ፡ የተሰጠው በሰማይም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው በምድርም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ከምድር ፡ በታች ፡ ኢየሱስ ፡ ነው በሁሉ ፡ ላይ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)