Loading
Singer
ምድር ፡ ለሰው ፡ ልጆች ፡ ተሰጥታለች ፡ አልፋ (፪x) ሁሉም ፡ በየሙያው ፡ ይላል ፡ ቀና ፡ ደፋ (፪x) ከዚህ ፡ ወዲያ ፡ አይባል ፡ ከዚያ ፡ በመለስ (፪x) ቅዱሱ ፡ ይቀደስ ፡ እርኩሱም ፡ ይርከስ (፪x) አይቶ ፡ ሰምቶ ፡ የለየ ፡ ነጸነት ፡ አለው እንስበከው ፡ እንጂ ፡ ጡንቻ ፡ አናሳየው ያሻውን ፡ ይከተል ፡ ሰው ፡ እንደገባው ሰይፋችን ፡ ይመለስ ፡ ወደ ፡ ሰገባው አዝ፦ ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ይንገሥ ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ይንገሥ ወርዶ ፡ የሚያድን ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ይሁን (ወርዶ ፡ የሚያድን ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ይሁን) ምድር ፡ ተባርካለች ፡ በሃይማኖት ፡ ብዛት (፪x) ህመሟ ፡ ባሰ ፡ እንጂ ፡ አንዱም ፡ አልፈወሳት (፪x) ምድር ፡ ተባርካለች ፡ በሃይማኖት ፡ ሃብት (፪x) እንትንና ፡ እንትን ፡ እንትን ፡ በሚሉት (፪x) አሁንም ፡ ይፈልቃል ፡ በየቀበሌው እናትና ፡ አባት ፡ አያት ፡ የሌለው አንዱ ፡ ካላዳነ ፡ አያድንም ፡ ሲሉ ወገኔ ፡ ተመለስ ፡ ይቅርብህ ፡ እልሁ አዝ፦ ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ይንገሥ ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ይንገሥ ወርዶ ፡ የሚያድን ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ይሁን (ወርዶ ፡ የሚያድን ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ይሁን) በስራ ፡ ይገለጥ ፡ የያዝነው ፡ እምነት (፪x) ሙታንም ፡ ይነሱ ፡ ይውጡ ፡ አጋንንት (፪x) ዳንኩኝ ፡ ተፈወስኩኝ ፡ ብለው ፡ ይመስክሩ (፪x) የሃይማኖት ፡ ፋርዳ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ቁም ፡ ነገሩ (፪x) የሚያድን ፡ እምነት ፡ የሚያደርስ ፡ ሠማይ ከሌለው ፡ ሰው ፡ አልፎ ፡ ሰርቶ ፡ አይበላም ፡ ወይ በሰላም ፡ እንደር ፡ አይረበሽ ፡ ሰፈር ድንበር ፡ አትለፉ ፡ ተዉ ፡ አንደፋፈር አዝ፦ ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ይንገሥ ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ይንገሥ ወርዶ ፡ የሚያድን ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ይሁን (ወርዶ ፡ የሚያድን ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ይሁን) ደርሶ ፡ ስም ፡ ለማጥፋት ፡ ወሬ ፡ አሉባልታ (፪x) ጭራሽ ፡ ይባል ፡ ብሎ ፡ በአስክሬን ፡ ጨዋት (፪x) ትዳርን ፡ አፋቶ ፡ ልጅ ፡ ከእናት ፡ ነጥሎ (፪x) ከቀዬ ፡ ከሰፈር ፡ ከማህበር ፡ አግልሎ (፪x) ከገነት ፡ ሊገባ ፡ እንዲያው ፡ መታሰቡ ቀርጥህን ፡ እወቀው ፡ አትደርስ ፡ ከአጠገቡ አሳደህ ፡ እሰረው ፡ ግደልልኝ ፡ ያለ ዲያቢሎስ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይደለ አዝ፦ ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ይንገሥ ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ይንገሥ ወርዶ ፡ የሚያድን ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ይሁን (ወርዶ ፡ የሚያድን ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ይሁን) የእኔ ፡ ይበልጣል ፡ ቢሉ ፡ ምንም ፡ ክፋት ፡ የለው (፪x) እኛ ፡ ማንስማማው ፡ ዛቻ ፡ ሲጀመር ፡ ነው (፪x) እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ ለሁሉም ፡ ይበቃል ምስክር ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ አያሻው ፡ ጠበቃ (፪x) እናንት ፡ የአምላክ ፡ ልጆች ፡ ከቶ ፡ አትታወኩ ሁሉም ፡ በየቋንቋው ፡ ይጩህ ፡ ወደአምላኩ የሁሉም ፡ ማንነት ፡ በተግባር ፡ ይታያል የኤልያስ ፡ አምላክ ፡ በእሳት ፡ ይለያል አዝ፦ ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ይንገሥ ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ይንገሥ ወርዶ ፡ የሚያድን ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ይሁን (ወርዶ ፡ የሚያድን ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ይሁን)