Loading
Singer
አዝ፦ ስምህ ፡ ይባረክ ፡ ዘለዓለም ፡ ስምህ ፡ ይባረክ (፪x) ተመስገን ፡ ኢየሱስ/ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ እኔም ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ (፪x) ለቅሶውን ፡ የሚሰማው ፡ አጥቶ ፡ ከሰው ፡ ህሊና ፡ ተረስቶ ደክሞ ፡ በዓልጋ ፡ እየማቀቀ ፡ ዕድሜው ፡ ዘመኑ ፡ አለቀ የተባለው ፡ ያ ፡ ሰው ፡ ዛሬ ፡ ይሄው ፡ ቆሟል አስኪ ፡ እዩት ፡ አልጋውን ፡ በትከሻው ፡ ይዟል ይህን ፡ የአደረገው ፡ ክብሩ ፡ የገነነ ኢየሱስ ፡ ይባረክ ፡ ደሃን ፡ የተለመነ አዝ፦ ስምህ ፡ ይባረክ ፡ ዘለዓለም ፡ ስምህ ፡ ይባረክ (፪x) ተመስገን ፡ ኢየሱስ/ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ እኔም ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ (፪x) አሳዳጅ ፡ እጅግ ፡ ጨካኝ ፡ ሰው አገር ፡ ምድሩ ፡ ሁሉ ፡ የሚያወቀው ጌታን ፡ እምርሮ ፡ ሚጠላ ፡ ለሕግ: ከልቡ፡ የቀና ድንገት ፡ ጌታ ፡ ደርሶ ፡ ይህን ፡ ሰው ፡ ሲነካው ሥሙ ፡ ጳውሎስ ፡ ሆነ ፡ ከዚያ ፡ ማን ፡ ይቻለው ወንጌልን ፡ በምድር ፡ በስልጣን ፡ ሰበከ ጀግና ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ጀግናውን ፡ ማረከ አዝ፦ ስምህ ፡ ይባረክ ፡ ዘለዓለም ፡ ስምህ ፡ ይባረክ (፪x) ተመስገን ፡ ኢየሱስ/ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ እኔም ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ (፪x) አፈር ፡ ለብሶ ፡ የሸተተ ፡ ህይወቱ፡ ኑሮው ፡ ተከተተ አልዓዛር ፡ ወየው ፡ በቃለት ፡ ከኃጢአት ፡ ተለየ ፡ በሞት ስትል ፡ ማሪያም ፡ አዝና ፡ እንባዋን ፡ እየዘራች ምነው ፡ ኢየሱስ ፡ በዚህ ፡ ቢኖር ፡ ኖሮ ፡ እያለች ተስፋ ፡ ቆርጣ ፡ ደክማ ፡ አልዓዛርን ፡ ጠራው ኢየሱስ ፡ በዚያ ፡ ሲደርስ፡ የድል ፡ ብርሃን ፡ በራ አዝ፦ ስምህ ፡ ይባረክ ፡ ዘለዓለም ፡ ስምህ ፡ ይባረክ (፪x) ተመስገን ፡ ኢየሱስ/ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ እኔም ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ (፪x) በመንገድ ፡ ወድቆ ፡ ሲለምን ፡ አካሉ ፡ ሁሉ ፡ ሲባክን ሰርቶ: ወይ: ደክሞ ፡ አይበላ ዘመኑን ፡ ሁሉ ፡ ሲጉላላ ቀኑ ፡ ደረሰና ፡ ኢየሱስ ፡ መጣለት ደጋግሞ ፡ እየጮኸ ፡ ተጣራ ፡ በእምነት የለማኙን ፡ጩኸት: ለይቶ: አደመጠ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ታሪኩን ፡ ለወጠ አዝ፦ ስምህ ፡ ይባረክ ፡ ዘለዓለም ፡ ስምህ ፡ ይባረክ (፪x) ተመስገን ፡ ኢየሱስ/ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ እኔም ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ (፪x) በሃኪም ፡ ገንዘቧን ፡ ጨርሳ ሃፍረት ፡ እንደ ፡ ሸማ ፡ ለብሳ ከሰው ፡ ከሃገሩ ፡ እየራቀች አስራ ፡ ሁለት ፡ ዓመት ፡ ማቀቀች የምስኪኖች ፡ ተስፋ ፡ በመንደሩ ፡ አለፈ ሊጐበኛት ፡ ፈቅዶ ፡ ሸክሟን ፡ አሳረፈ ኧረ ፡ ምን ፡ ይባላል ፡ ምንስ ፡ ይመለሳል እውነትም ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ለምስኪን ፡ ይደርሳል አዝ፦ ስምህ ፡ ይባረክ ፡ ዘለዓለም ፡ ስምህ ፡ ይባረክ (፪x) ተመስገን ፡ ኢየሱስ/ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ እኔም ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ (፪x)